የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በከተማ አስተዳደሩ በተደረገው የትምህርት ቤት አመራሮች ውድድር ወደ ርዕሰ መምህርነት ለመጡ የትምህርት ቤት አመራሮች ስልጠና መሰጠት ጀመረ፡፡

by | ዜና

(ቀን ጥር 27/2016 ዓ.ም)  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  ትምህርት ቢሮ በከተማ አስተዳደሩ በተደረገው  የትምህርት ቤት አመራር ውድድር ወደ ርዕሰ መምህርነት ለመጡ የትምህርት ቤት አመራሮች  ለስድስት ቀናት የሚቆይ ስልጠና መስጠት ጀምራል።

ስልጠናው በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን የሚሰጥ ሲሆን በስልጠና መድረኩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ  የትምህርት ጥራትን ለማምጣትና  ትውልድን በተገቢው ሁኔታ ለማነጽ  ከዚህ በፊት በሚፈለገው ደረጃ ውጤት እንዳይምጣ ካዳረጉ ጉዳዮች መካከል የትምህርት አመራሩ  በቁርጠኝነት  ተቀናጅቶ አለመስራት ነዉ ያሉ ሲሆን ይህንን ክፍተት ለመሙላትና በትምህርት ዘርፍ ውጤት ለማስመዝገብ  በውድድር ወደ ርዕሰ መምህርነት  የመጡ የትምህርት አመራሮች በቁርጠኝነትና በብቃት  መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡

ሀላፊዉ አክለዉም ትውልድን ለመምራት የበቃና የነቃ  እንዲሁም ተቀናጅቶና ተሰናስሎ መስራት የሚችል የትምህርት አመራር  ያስፈልጋል ያሉ ሲሆን ቢሮ ያዘጋጀው የስልጠና መርሀ ግብር በአዲስ የተደራጀዉን የትምህርት ቤት አመራር አቅም ለማጎልበት ያግዛል በማለት ለስልጠናዉ መሰካት አስተዋጽዎ ላበረከቱ ለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምሁራንና ለኮሜርስ ካምፓስ  ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ድንቃለም ቶሎሳ የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል የትምህርት አመራሩ ሚና ከፍተኛ ነዉ ያሉ ሲሆን በብቃት መስራት ለተሻለ ውጤት መመዝገብ ፋይዳው የጎላ መሆኑን በመጥቀስ በውድድሩ የመምህራን ማህበር በየደረጃዉ በኮሚቴነት መስራቱን ጠቅሰዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ አሊ ከማል ስልጠናው ለተከታታይ ስድስት ቀናት የሚሰጥ መሆኑን በመግለጽ ብቁ ዜጋ ለማፍራት በትጋት መስራት ከትምህርት አመራሩ ይጠበቃል ብለዋል፡፡

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

https://twitter.com/aacaebc

SITE VISITORS

  • 0
  • 184
  • 249
  • 2,420
  • 8,972
  • 243,954
  • 243,954