የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሰራተኞች ስልጠና መድረክ “አገልጋይና ስልጡን ሲቪል ሰርቫንት ለኢትዮጵያ ብልፅግና!” በሚል መሪ ቃል መሰጠት ጀመረ፡፡

by | ዜና

(ቀን ጥር 24/2016 ዓ.ም)  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር   ትምህርት ቢሮ ሰራተኞች  ስልጠና መድረክ  የተጀመረ ሲሆን  በስልጠናዉ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ  ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የቢሮ ማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞች ተገኝተዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ስልጠናዉ ለሁለት ቀናት እንደሚሰጥና በስልጠናዉ ላይ በሁለቱም ቀናት የተለያዩ ሰነዶች የሚቀርቡ በመሆኑ ሰራተኞች በአግባቡ መከታተልና የነቃ ተሳትፎ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸዉ በማግለጽ ስልጠናዉ አገልጋይና ስልጡን ሲቪል ስርቪስ ለመፍጠር ያግዛል ብለዋል፡፡

የመጀመሪያው የስልጠና ሰነድ  በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ በሆኑት በአቶ  አሊ ከማል በመቅረብ ላይ ይገኛል፡፡

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

https://twitter.com/aacaebc

SITE VISITORS

  • 0
  • 28
  • 222
  • 1,582
  • 6,362
  • 214,623
  • 214,623