የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ድጋፍ ክትትል ምዘና ዳይሬክቶሬት የ2016ዓ.ም የ6 ወር የሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ምዘና ማካሄዱን አስታወቀ፡፡

by | ዜና

(ቀን ጥር 21/2016 ዓ.ም)  ምዘናው በዋናነት በቢሮው በሚገኙ ዳይሬክቶሬቶች የተካሄደ ሲሆን በቀጣይ በክፍለከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤቶችና በተመረጡ ትምህርት ቤቶች የሚካሄድ መሆኑን ከስራ ክፍሉ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ድጋፍ ክትትል ምዘና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዳዊት ከበደ የምዘናውን አላማ አስመልክቶ በሰጡት አስተያየት ከቢሮ ጀምሮ በየደረጃው ባሉ መዋቅሮች የአገልግሎት አሰጣጡም ሆነ የመልካም አስተዳደር ተግባሩ ያለበትን የአፈጻጸም ደረጃ ለመፈረጅና የሚታዩ ችግሮችን መሰረት በማድረግ የተሻለ ስራ ለመስራት ታስቦ መካሄዱን ገልጸዋል፡፡

ዳይሬክተሩ አክለውም ምዘናው በስራ ክፍሎች መካከል ጤናማ ውድድር ከመፍጠሩ ባሻገር የተቃሙን አፈጻጸም ማሳደግ የሚያስችል መሆኑን ገልጸው ዳይሬክቶሬቱ ቀደም ሲል በሁሉም ስራ ክፍሎች ድጋፍና ክትትል ስራ መስራቱንም አስገንዝበዋል፡፡

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

https://twitter.com/aacaebc

SITE VISITORS

  • 0
  • 27
  • 222
  • 1,581
  • 6,361
  • 214,622
  • 214,622