የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ጉዳዮች ትግበራ ዳይሬክቶሬት ከክፍለከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት የልዩ ፍላጎትና ዘርፈብዙ ጉዳይ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች ጋር ውይይት አካሄደ፡፡

ውይይቱ በዋናነት አዲሱን የመሰረታዊ የስራ ሂደት ለውጥ ማሻሻያ ጥናት መሰረት አድርጎ  በቅርቡ ተግባራዊ ከተደረገው አደረጃጀት ጋር በተገናኘ በዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ጉዳዮች ትግበራ ዳይሬክቶሬት በሚከናወኑ ተግባራት ዙሪያ በመወያየት በቀጣይ የተሻለ ስራ ለመስራት ታስቦ መዘጋጀቱን ከስራ ክፍሉ የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡

በውይይቱ መክፈቻ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ ባስተላለፉት መልዕክት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት ልማት ስራውን ውጤታማ ለማድረግ አዲስ አደረጃጀት አስጠንቶ ወደተግባር መግባቱን ጠቁመው የዘርፈብዙና ቀዳማይ ልጅነት ጉዳዮች ዳይሬክተር በአዲስ መልክ ከተደራጁና አላማ ፈጻሚ ከሆኑ ስራ ክፍሎች አንዱ መሆኑን በመግለጽ ከቢሮው ጀምሮ በክፍለከተማና ወረዳ በዘርፉ የተመደቡ ባለሙያዎች የተጣለባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት እንዲችሉ  በአደረጃጀቱ ዙሪያ ውይይት መካሄዱ ተገቢ ተግባር መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ጉዳዮች ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ በላይነሽ ይሻው በበኩላቸው በአዲሱ አደረጃጀት መሰረት በዳይሬክቶሬቱ የቀዳማይ ልጅነት ትምህርት ክብካቤ፣የስርአተ ጾታ ጉዳይ ክትትልና ድጋፍ እንዲሁም የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ዘርፎችን መሰረት በማድረግ የተለያዩ ተግባራት እንደሚከናወኑ ገልጸው የዛሬው ውይይት በዘርፉ በሚከናወኑ ተግባራት ዙሪያ  የጋራ ግንዛቤ በመያዝ በቀጣይ ውጤታማ ስራ ለመስራት ታስቦ መዘጋጀቱን አስረድተዋል፡፡

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 187
  • 249
  • 2,423
  • 8,975
  • 243,957
  • 243,957