የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ለአቅመ ደካሞች እና አረጋውያን የማዕድ ማጋራት መርሀ-ግብር አከናወነ።

by | ዜና

(ቀን ታህሳስ 27/2016 ዓ.ም)  የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 እና 3  ስር ለሚገኙ አቅመ ደካሞች እና አረጋውያን የማዕድ ማጋራት መርሀ-ግብር አከናወነ።

                       

በማዕድ ማጋራት መርሀ-ግብሩ  ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት  ቢሮ  ሃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ እንኳን አደረሳችሁ በማለት በቦታው ለተገኙ አካላት ቢሮ ከጎናቸው እንደቆመ በመግለጽ በቀጣይም ሰው ተኮር ስራዎችን መሰረት በማድረግ በትኩረት የሚሰራ መሆኑን ገልጸው በዓሉ ያማረና የደመቀ እንዲሆን ተመኝተዋል ።

የጉለሌ ክፍለ ከተማ የዲሞክራሲ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ይከበር ስማቸው በበኩላቸው ትምህርት ቢሮ ከመማር ማስተማሩ ጎን ለጎን የማህበረሰብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በርካታ ስራዎችን  እየሰራ በመሆኑ ምስጋና አቀርባለሁ በማለት በቦታው ለተገኙ አካላት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል ።

                                       

በማዕድ ማጋራቱ ስነ-ስርአት ላይ የትምህርት ቢሮ የማኔጅመንት አባላት ፣ የጉለሌ ክፍለ ከተማ እና የወረዳ  አመራሮች ተገኝተዋል ።

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 70
  • 222
  • 1,624
  • 6,404
  • 214,665
  • 214,665