የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ለግል ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በጨዋታ የማስተማር ስነ-ዘዴ ላይ ስልጠና ሰጠ::

by | ዜና

(ቀን ታህሳስ 20/2016 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  በ 11ዱ ክፍለ ከተሞች  በ9 ስልጠና መስጫ ጣቢያዎች ላይ  ለግል የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መምህራን በጨዋታ የማስተማር ስነ-ዘዴ ላይ ትኩረት ያደረገ ስልጠና መስጠት ጀምሯል::

በጨዋታ የማስተማር ስነ-ዘዴ ሙሉ ለሙሉ የሚታወቅ ባይሆንም ከዚህ በፊት በመንግስት ትምህርት ቤቶች ተሰጥቶ ውጤታማነቱ መረጋገጡን ያብራሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቀዳማይ ልጅነት ጉዳዮች ትግበራ ዳይሬቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ በላይነሽ የሻው በጨዋታ የማስተማር ስነ-ዘዴው እየተከተልን ያለውን ተማሪ ተኮር የማስተማር ስነ-ዘዴ ውጤታማ የሚያደርግ እንዲሁም ተማሪዎችን በማነቃቃት በአይምሮ ፣ በስነ-ልቦናና በአካል ዝግጁ ሆነው ወደ 1ኛ ደረጃ ትምህርት እንዲሻገሩ ያደርጋል ብለዋል ::

አያይዘውም የትምህርት ጥራትን በዘላቂነት ለማስጠበቅ ህፃናቶችን በጨዋታ የማስተማር ስነ-ዘዴ ዋናውና  መሰረታዊ ጉዳይ መሆኑን ተናግረዋል ::

ስልጠናው በሁሉም ክፍለ ከተሞች ለሚገኙ ሁሉም የግል  ቅድመ 1ኛ ደረጃ መምህራን በቀጣይነት የሚሰጥ ሲሆን ቀደም ሲል የመንግስት ትምህርት ቤት መምህራንን ለማሰልጠን የአሰልጣኞች ስልጠና በወሰዱ መምህራን ስልጠናው እንደሚሰጥና ለስልጠናው የሚያስፈልጉ የፅህፈት መሳሪያዎችና የተለያዩ ግብአቶች አቅርቦትም በቢሮው እንደሚሸፈን ያገኝነው መረጃ ያሳያል ::

 

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 30
  • 222
  • 1,584
  • 6,364
  • 214,625
  • 214,625