የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ቡድን ለቢሮው ባለሙያዎች የክህሎት ማሻሻያ ስልጠና በመስጠት ላይ መሆኑን አስታወቀ፡፡

by | ዜና

(ቀን ታህሳስ 18/2016 ዓ.ም) ስልጠናው  ቀደም ሲል በቢሮ ደረጃ የተካሄደ የስልጠና ፍላጎት ዳሰሳን መሰረት አድርጎ ከባለሙያዎች በተሰበሰበ መረጃ መሰረት የሚሰጥ ሲሆን ስልጠናውም ለሁሉም የቢሮው ሰራተኞች በዙር እንደሚሰጥ ከስራ ክፍሉ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ቡድን መሪ አቶ ታዬ ወልደ ኪዳን ስልጠናው በዋናነት ከኤክስ ኤል እንዲሁም ከቴክኖሎጂ መጠቀሚያ ቁሳቁሶች ጋር በተገናኘ የሚያጋጥሙ መለስተኛ ብልሽቶችን ማስተካከል እንዲችሉ የሚያግዛቸውን ክህሎት እንዲያዳብሩ ታስቦ መዘጋጀቱን ገልጸው ባለሙያዎቹ በስልጠናው ያገኙትን ግንዛቤ መሰረት በማድረግ ለተገልጋዩ በቴክኖሎጂ የተደገፈ አገልግሎት በመስጠት የቢሮውን ተልዕኮ ማሳካት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል፡፡

በስልጠናው የቢሮው የሲስተም ባለሙያ ወይዘሮ ፍሬሕይወት ገብረአብ ከኤክስ ኤል ጋር የተገናኘ ስልጠና በመስጠት ላይ ሲገኙ ከጥገና እና ተዛማጅ ጉዳዮች ጋር በተገናኘ ደግሞ የጥገና ባለሙያው አቶ ስሜነህ ተመስገን ስልጠናውን በመስጠት ላይ ይገኛሉ፡፡

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 30
  • 222
  • 1,584
  • 6,364
  • 214,625
  • 214,625