የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት መረጃ ስርዓት ስራ አመራር ቡድን ለወረዳ የመረጃ ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ።

by | ዜና

(አዲስ አበባ ህዳር 28 ቀን 2016 ዓ.ም) ስልጠናው ከኢፌድሪ ትምህርት ሚኒስቴር የተላከ የ2016 ዓ.ም የትምህርት መረጃ መሙያ ቅጽ አሞላልን  በተመለከተ የተሰጠ ሲሆን ሰልጣኞቹ በስልጠናው ያገኙትን ግንዛቤ መሰረት በማድረግ ጥራቱን የጠበቀ መረጃ ማደራጀት እንደሚጠበቅባቸው ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት መረጃ ባለሙያ አቶ ጋሻው አክሊሉ ከኢፌድሪ ትምህርት ሚኒስቴር የተላከ የትምህርት መረጃ መሰብሰቢያ ቅጽ አሞላልን በተመለከተ ስልጠና የሰጡ ሲሆን ቅጹ በዋናነት የትምህርት ቤቶችን አጠቃላይ መረጃን ከማካተቱ ባሻገር የተማሪ ፣ የመምህር፣ የርዕሳነ መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞችን መረጃ በአግባቡ መሙላት እንዲቻል ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ጠቁመው በየወረዳው የሚገኙ የመረጃ ባለሙያዎች በቅጹ መሰረት  መረጃዎችን በመሙላት ለሚመለከተው አካል መላክ እንደሚጠበቅባቸው አስታውቀዋል።

የትምህርት መረጃ በትምህርት ስርዓት ውስጥ እየተከናወኑ ያሉ ተግባራት ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኙም ሆነ ከዘርፉ ጋር በተገናኘ በየደረጃው ለሚወሰኑ ውሳኔዎች መሰረት በመሆኑ የወረዳ ባለሙያዎች ትክክለኛ መረጃ ማደራጀት እንደሚገባቸው የቢሮው የትምህርት መረጃ ባለሙያ አቶ ሀይለማርያም ቻለው አስገንዝበዋል።

 

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 27
  • 222
  • 1,581
  • 6,361
  • 214,622
  • 214,622