የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ ጋር በመተባበር ለአምስት ቀን ሲሰጥ የቆየውን የአሰልጣኞች ስልጠና በዛሬው እለት አጠናቀቀ፡፡

by | ዜና

(ህዳር 14 ቀን 2016 ዓ.ም) የአሰልጣኞች ስልጠናው ከቢሮ ጀምሮ እስከ ትምህርት ቤት ካሉ መዋቅሮች ለተውጣጡ ባለሙያዎች ቡድን መሪዎች አስተባባሪዎች በሁለት ቡድን ለ68 ሰልጣኞች የተሰጠ  ሲሆን ዳይሬክተሮች አስተባባሪዎችና ቡድን መሪዎች አንድ ላይ እንዲሁም ባለሙያዎች በሌላ ቡድን የአሰልጣኞች ስልጠናውን እንዲወስዱ ተደርጉዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቢሮ ኃላፊ አማካሪ ወይዘሮ አበበች ነጋሽ  በአሰልጣኞች ስልጠናው ማጠቃለያ ባስተላለፉት መልዕክት በትምህርት ሴክተሩ የሚሰጠው አገልግሎት የተገልጋዩን እርካታ ታሳቢ ያደረገ እንዲሆን  የስልጠናው ተሳታፊዎች በየደረጃው ግንዛቤ መፍጠር እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል፡፡

በአሰልጣኞች ስልጠናው መርሀ ግብሩ የቢሮው የለውጥና መልካም አስተዳደር ባለሙያ ወይዘሪት ሙሉ አንዳርጌ የተገልጋይ ተኮር አገልግሎት አሰጣጥ ፤ የተግባቦት ችሎታ ፤ የስሜት ብልህነት ፤ ሙያዊ ስነ-ምግባር እና የስልጠና አዘገጃጀትና ግምገማን በተመለከተ ለባለሙያዎች ስልጠና የሰጡ ሲሆን የለውጥና መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ አቶ ዳዊት ከበደ በበኩላቸው ዜጋ ተኮር አገልግሎት አሰጣጥ ፤ የእውቀት ስራ አመራር ፤ የተቋማዊ ባህል ግንባታን እና የስልጠና አዘገጃጀትና ግምገማን በተመለከተ ለቡድን መሪዎችና አስተባባሪዎች ስልጠና መስጠታቸው ቀደም ብሎ መገለጹ ይታወቃል፡፡

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 30
  • 222
  • 1,584
  • 6,364
  • 214,625
  • 214,625