(ህዳር 10 ቀን 2016 ዓ.ም) የአሰልጣኞች ስልጠናው ከቢሮ ጀምሮ እስከ ትምህርት ቤት ካሉ መዋቅሮች ለተውጣጡ ባለሙያዎች ቡድን መሪዎችና አስተባባሪዎች በሁለት ቡድን በመሰጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን ዳይሬክተሮች አስተባባሪዎችና ቡድን መሪዎች አንድ ላይ እንዲሁም ባለሙያዎች በሌላ ቡድን የአሰልጣኞች ስልጠናውን በመሰልጠን ላይ ይገኛሉ፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የለውጥና መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዳዊት ከበደ የአሰልጣኞች ስልጠናውን አላማ አስመልክቶ በሰጡት አስተያየት በትምህርት ሴክተሩ በሚገኙ ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥንም ሆነ የአመራር ስርዓትን ለማሻሻል እና በተቋማቱ እንዴት ጥሩ የባህል ግንባታ መፍጠር እንደሚቻል ግንዛቤ እንዲኖር ታስቦ ስልጠናው መዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡
ዳይሬክተሩ አክለውም ቀደም ሲል የአዲስ አበባ ፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ በከተማ ደረጃ ከተለያዩ ተቃማት ለተውጣጡ ሰልጣኞች የሰጠውን ስልጠና መሰረት በማድረግ እና ከትምህርት ሴክተሩ ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማጣጣም ስልጠናው መዘጋጀቱን አስታውቀዋል፡፡
የቢሮው የለውጥና መልካም አስተዳደር ባለሙያ ወይዘሪት ሙሉ አንዳርጌ የተገልጋይ ተኮር አገልግሎት አሰጣጥ ፤ የተግባቦት ችሎታ ፤ የስሜት ብልህነት ፤ ሙያዊ ስነ-ምግባር እና የስልጠና አዘገጃጀትና ግምገማን በተመለከተ ለባለሙያዎች ስልጠና በመስጠት ላይ የሚገኙ ሲሆን የለውጥና መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተሩ አቶ ዳዊት ከበደ በበኩላቸው ዜጋ ተኮር አገልግሎት አሰጣጥ ፤ የእውቀት ስራ አመራር ፤ የተቋማዊ ባህል ግንባታን እና የስልጠና አዘገጃጀትና ግምገማን በተመለከተ ለቡድን መሪዎችና አስተባባሪዎች ስልጠና እንደሚሰጡ ከወጣው መርሀ-ግብር ለማወቅ ተችሉዋል፡፡
የአሰልጣኞች ስልጠናው ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ አምሰት ቀን የሚቆይ ሲሆን በቀጣይ ሰልጣኞቹ ከቢሮ ጀምሮ በክፍለ ከተማ ወረዳ እና ትምህርት ቤቶች ተመሳሳይ ስልጠና የሚሰጡ ይሆናል፡፡
0 Comments