ሱፐር ቪዥኑ በከተማው በሚገኙ የመንግስትና የግል አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ያለው የሬዲዮ ትምህርት አተገባበር ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝ በማየት በቀጣይ ከትምህርት አገልግሎቱ ተማሪዎች የሚፈለገውን እውቀት ማግኘት እንዲችሉ ታስቦ መካሄዱን በአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የትምህርት መዝና ኛ ፕሮግራም ዝግጅትና የሬዲዮ ትምህርት ቀረጻና ስርጭት ቡድን መሪ አቶ አብይ ተፈራ አስታውቀዋል።
ቡድን መሪው አክለውም በአዲስ አበባ አዲሱን ስርአተ ትምህርት መሰረት በማድረግ በአማርኛ እና አፋን ኦሮሞ ቋንቋዎች የሬዲዮ ትምህርት ስክሪፕት ተዘጋጅቶ ለትምህርት ቤቶች መላኩን ገልጸው ሱፐርቪዥኑ በየትምህርት ቤቶቹ ያለውን የሬዲዮ ትምህርት አሰጣጥ ጠንካራ ጎኖችም ሆነ መሻሻል የሚገባቸውን ጉዳዮች መሰረት በማድረግ በቀጣዩ የትምህርት አመት የተሻለ ስራ ለመስራት እንደሚረዳም አስረድተዋል። የሱፐርቪዥኑ ተሳታፊ የትምህርት ባለሙያዎች በአብዛኞቹ ትምህርት ቤቶች ያለው የሬዲዮ ትምህርት አገልግሎት የሚበረታታ ቢሆንም በአንዳንድ የግል ትምህርት ቤቶች ለሬዲዮ ትምህርት የሚሰጠው ትኩረት አነስተኛ በመሆኑ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ተገቢውን ክትትል በማድረግ ተቋማቱ አገልግሎቱን በአግባቡ እንዲተገብሩ ግፊት ማድረግ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።
0 Comments