የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም ለፍትሀዊነት(GEQIP-E) በአከባቢያዊና ማህበራዊ ጥበቃ አስተዳደር ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራትን ገመገመ።

by | ዜና

(ህዳር 8 ቀን 2016 ዓ.ም) በፕሮግራሙ ተግባራዊ እንዲሆኑ ከተያዙ እቅዶች መካከል የአከባቢያዊና ማህበራዊ ጥበቃ ዘርፍ አንዱ እንደመሆኑ ፕሮግራሙ ከተጀመረበት 2011ዓ.ም ጀምሮ ከቢሮ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ ጉዳዩ ለሚመለከታቸው አካላት የግንዛቤ ማስጨባጫ ስልጠና ሲሰጥ መቆየቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም ለፍትሀዊነት(GEQIP-E) ሪጅናል ኮርድኔተር አቶ አሸናፊ ከበደ ገልጸው የዛሬው መርሀ ግብር በዘርፉ የተከናወኑ ተግባራት ምንደረጃ ላይ እንደሚገኝ ከቢሮ ጀምሮ ክፍለከተማ፣ወረዳና በትምህርት ቤት ደረጃ በጉዳዩ  ዙሪያ ከሚ ሰሩ አካላት ጋር በጋራ ለመገምገም ታስቦ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል።

አቶ አሸናፊ አክለውም በፕሮግራሙ በእቅድ ከተካተቱ ተግባራት መካከል የስርአተ ጾታ እና የስነምግባርና ጸረ ሙስና ጉዳዮች እንደሚገኙ በመጥቀስ በመርሀ ግብሩ ከነዚሁ ተግባራት ጋር በተገና ኘ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስ ልጠና እንደሚሰጥ ጠቁመው በስራ ክፍሎቹ ተግባራቱ በተያዘላቸው እቅድ መሰረት መከናወናቸውን በፕሮጀክት ማስተባበሪያው አማካይነት የመከታተልና ወቅቱን የጠበቀ ግብረ መልስ የመስጠት ስራ እንደሚሰራ ገልጸዋል።

በመርሀ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ በላይነሽ የሻው በትምህርት ቤቶችና አከባቢ የሚፈጸም ጾታዊ ጥቃትን ለመከላከልና ምላሽ ለመስጠት በትምህርት ሚኒስቴር የወጣ መመሪያ ያቀረቡ ሲሆን በነገው መርሀ ግብር የቢሮው የስነ-ምግባርና ጸረሙስና ዳይሬክተር አቶ  አስራት ሽፈራው ከስነምግባርና ጸረ ሙስና ተግባር ጋር በተገና ኘ ስልጠና እንደሚሰጡ ከወጣው ፕሮግራም ለማወቅ ተችሏል።

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 205
  • 158
  • 7,078
  • 31,331
  • 147,475
  • 147,475