የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት አመራርና መረጃ ቡድን ለክፍለ ከተማ የትምህርት ቴክኖሎጂና መረጃ ቡድን መሪዎችና አይ ሲቲ ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ።

by | ዜና

(ህዳር 8 ቀን 2016 ዓ.ም) ስልጠናው በዋናነት በትምህርት ሴክተሩ ከአጠቃላይ የትምህርት  ጋር በተገናኘ ያሉ መረጃዎችን በማጥራት ጥራቱን የጠበቀና ተአማኒነት ያለው መረጃ ለሚመለከተው ባለድርሻ አካል ተደራሽ ለማድረግ ታስቦ መሰጠቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂና መረጃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ዳኜ አ ስታውቀዋል።

የቢሮው የትምህርት አመራርና መረጃ ቡድን መሪ አቶ ደስታ አብረሀም በበኩላቸው የስልጠናው ተ ሳታፊዎች ቀደም ሲል ተመ ሳሳይ ስልጠና መውሰዳቸውን ጠቁመው ሰልጣኞቹ በስልጠናው ያገኙትን ግንዛቤ መሰረት በማድረግ ለ2015ዓ.ም አመታዊ የትምህርት መረጃ መጽሄት ዝግጅት የሚሆን ግብአት ከማቅረብ ባሻገር የ2016ዓ.ም አጠቃላይ የትምህርት መረጃን በአግባቡ አደራጅተው ለቢሮው ሪፖርት ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።

በትምህርት ሴክተሩ በቴክኖሎጂ የተደገፈ መረጃ ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተደራሽ ለማድረግ እንዲቻል የቢሮው የአይ ሲቲ ባለሙያዎች ተገቢውን የድጋፍና ክትትል ስራ በመስራት ላይ እንደሚገኙ የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቡድን መሪ አቶ ታዬ ወልደኪዳን ገልጸዋል።

በአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማሻሻያ ፕሮግራም ለፍትሀዊነት(GEQIP-E) በእቅድ ከተያዙ ተግባራት መካከል አንዱ በትምህርት መረጃ ስርአት ዙሪያ ለሚመለከታቸው አካላት ግንዛቤ መፍጠር መሆኑን በትምህርት ቢሮ የፕሮግራሙ ሪጅናል ዳይሬክተር አቶ አሸናፊ ከበደ ገልጸው ፕሮግራሙ በአግባቡ ተግባራዊ መሆኑን በየደረጃው የመከታተልና ወቅታዊ ግብረ መልስ የመስጠት ስራ እንደሚሰራ አስታውቀዋል።

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 204
  • 158
  • 7,077
  • 31,330
  • 147,474
  • 147,474