የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት ስራ አመራርና መረጃ ቡድን ለክፍለከተ መረጃ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች ሲሰጥ የቆየውን ስልጠና አጠናቀቀ፡፡

by | ዜና

(ህዳር 3/2016 ዓ.ም) ስልጠናው በዋናነት ከኢፌድሪ ትምህርት ሚኒስቴር በወረደ የ2016 ዓ.ም የመረጃ መሰብሰቢያ ቅጽ አሞላልና በ2015 ዓ.ም አመታዊ የትምህርት መረጃ መጽሄት ለማዘጋጀት በሚያስፈልጉ ግብአቶች ዙሪያ በተግባር ተደግፎ መሰጠቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት ስራ አመራርና መረጃ ቡድን መሪ አቶ ደስታ አብረሀም ገልጸዋል።

በመርሀ ግብሩ የቢሮው የትምህርት መረጃ ባለሙያ ወይዘሮ ሸምሲያ የትምህርት መረጃ ጽንሰ ሀሳብና አስፈላጊነትን በተመለከተ ስልጠና የሰጡ ሲሆን የስልጠናው ተሳታፊዎችም የተለያዩ አስተያየቶችን እና ጥያቄዎችን አቅርበው ምላሽ ተሰቷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂና መረጃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ዳኜ በስልጠናው ማጠቃለያ ባስተላለፉት መልዕክት  በትምህርት ሴክተሩ  የሚሰበሰብ መረጃ  በዘርፉ  ለሚወሰን የትኛውም ውሳኔም ሆነ ተገቢውን በጀት ለመመደብ እንደ መነሻ የሚወሰድ በመሆኑ የስልጠናው ተሳታፊዎች ከኢፌድሪ ትምህርት ሚኒስቴር በወረደው የ2016 ዓ.ም የመረጃ መሰብሰቢያ ቅጽ መሰረት ጥራቱን የጠበቀና ተአማኒነት ያለው መረጃ በመሙላት ለሚመለከተው አካል ሪፖርት ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል፡፡

 

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 0
  • 175
  • 2,114
  • 9,135
  • 234,185
  • 234,185