የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ትምህርት ትግበራ ዳይሬክቶሬት በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ስልጠና ሰጠ።

by | ዜና

(ህዳር 2/2016 ዓ.ም) ስልጠናው የቀዳማይ ልጅነት ክብካቤና ትምህርትን በቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በምን መልኩ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚቻል ለክፍለ ከተማ የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት አስተባባሪዎች፣ቡድን መሪዎችና ከተመረጡ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ አስተባባሪዎች መዘጋጀቱን ከዳይሬክቶሬቱ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ስልጠናውን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቀዳማይ ልጅነት ክብካቤና ትምህርት መምህር ተባባሪ ፕሮፌሰር  ይግዛው አየለ (ዶክተር)መስጠታቸውን የቢሮው የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ በላይነሽ ይሻው ገልጸው የስልጠናው ተሳታፊዎች በስልጠናው ያገኙትን ግንዛቤ መሰረት በማድረግ በትምህርት ተቋማቱ በዕውቀት ላይ የተመሰረተ የድጋፍና ክትትል ስራ መስራት እንደሚጠበቅባቸውም አስረድተዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቀዳማይ ልጅነት ክብካቤና ስልጠና ባለሙያ ወይዘሮ ፍሬህይወት በቀለ በበኩላቸው ከቢሮው የስርአተ ትምህርት ማበልጸግና ትግበራ ዳይሬክቶሬት ጋር በጋራ በመሆን የአዲሱን የቅድመ አንደኛ ደረጃ ስርአተ ትምህርት ይዘትና አተገባበር በተመለከት ለተሳታፊዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መሰጠቱን ጠቁመው ሰልጣኞቹም ከስርአተ ትምህርቱ ይዘት ጋር በተገናኘ ያገኙትን ግንዛቤ መሰረት አድርገው በትምህርት ቤቶቹ ተገቢውን ክትትል ማድረግ እንዲችሉ የሚያግዝ መሆኑንም አስታውቀዋል።

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 0
  • 175
  • 2,114
  • 9,135
  • 234,185
  • 234,185