የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የምስጋና መርሀ-ግብር አካሄደ።

by | ዜና

(ህዳር 1/2016 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2015 በጀት ዓመት ባስመዘገበው የላቀ አፈፃፀም ሽልማት የተበረከተለት መሆኑን ተከትሎ የምስጋና መርሀ-ግብር አካሄደ።

ቢሮው  በከተማ አስተዳደሩ ስር ከሚገኙ የካቢኔ አባል ከሆኑ ሴክተር መስሪያ ቤቶች 3ኛ በመውጣቱ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ክብርት ከንቲባ የመኪና እና የምስጋና የምስክር ወረቀት የተሰጠው መሆኑ ለቀጣይ ስራ መነሳሳትን የሚፈጥር መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጽፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ ገልፀዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ በ2015 በጀት ዓመት  የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ተቋማት የከተማ አስተዳደሩ በሰጠው እውቅና የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት  ቢሮ እውቅና በማግኘቱ የተስማቸውን ታላቅ ደስታ በመግለጽ  እውቅናው ለድካማችን ካሳ እና ለቀጣይ ስራ መነሳሳትን የሚፈጥር በመሆኑ ለዚህ ውጤት መመዝገብ አስተዋፅዎ ላደረጋችሁ አካላት በሙሉ  ምስጋና አቀርባለሁ ብለዋል።

በምስጋና መርሀ-ግብሩ በየደረጃው የሚገኙ የትምህርት አመራሮች፣ የትምህርት ዘርፉን ያገለግሉ የነበሩ የቀድም አመራሮች  ፣ የመምህራን ማህበር ፣ የወተማ አባላትና የትምህርት ቢሮ ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል።

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 179
  • 249
  • 2,415
  • 8,967
  • 243,949
  • 243,949