የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት ቤት መሻሻልና ግብአት ዳይሬክቶሬት በትምህርት ተቋማት ለሚደረግ ድጋፍና ክትትል ባዘጋጀው ቼክ ሊስት ዙሪያ ኦረንቴሽን ሰጠ፡፡

by | ዜና

(ጥቅምት 30/2016 ዓ.ም)   ኦረንቴሽኑ የተሰጠው ለክፍለከተማ የትምህርት ቤት መሻሻል አስተባባሪዎች ፤ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች ሲሆን ቼክሊስቱ በየትምህርት ቤቱ በ2ኛ ሩብ አመት የሚከናወኑ ተግባራትን መሰረት አድርጎ የተዘጋጀ መሆኑን በመርሀ-ግብሩ ተገልጻል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት ቤት መሻሻልና ግብአት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ቀጸላ ፍቅረማርያም ኦረንቴሽኑን በሰጡበት ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት ቼክሊስቱ በዋናነት የመጽሀፍ ፤ ደብተርና ደንብ ልብስ ስርጭት ያለበትን ሁኔታ መሰረት አድርጎ ከመዘጋጀቱ ባሻገር በየትምህርት ቤቱ ከከተማ ግብርና ጋር በተገናኘ በተለይም የጓሮ አትከልት ልማት እንዲሁም የዶሮና ከብት እርባታን ጨምሮ የንብ ማነብ ስራዎች ያሉበትን ደረጃ ለማወቅ ታስቦ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል፡፡

ዳይሬክተሩ አክለውም ኦረንቴሽኑን የወሰዱ ባለሙያዎች በተዘጋጀው ቼክሊስት መሰረት ከሰኞ ጀምሮ ለተከታታይ አምስት ቀናት በየትምህርት ቤቱ በመገኘት መረጃ እንደሚሰበስቡ ጠቁመው መረጃው ተጠምሮ ለሚመለከተው አካል ሪፖርት የሚደረግ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 0
  • 205
  • 6,046
  • 31,180
  • 147,475
  • 147,475