የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ጋር በጋራ በመሆን የ2016 የትምህርት ዘመን የትምህርት አጀማመር ሱፐርቪዥን ግኝትና የ2015 ዓ.ም የኢንስፔክሽን ውጤት ላይ የውይይት መድረክ አካሄደ ።

by | ዜና

(ጥቅምት 23/2016 ዓ.ም)  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ጋር በጋራ በመሆን የ2016 የትምህርት ዘመን የትምህርት አጀማመር ሱፐርቪዥን ግኝት ፣ የ2015 ዓ.ም የኢንስፔክሽን ውጤት .፣  የ 2016 በጀት ዓመት የሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ላይ ውይይት አድርገዋል ።

የትምህርት ሥራ አዳጊ ፈታኝና ሀገርና ወገንን የሚደግፍ የሀገር ብልፅግና መሰረት ነው ያሉት የትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ስራ አሰኪያጅ  አቶ ዳኝው ገብሩ  በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በርካታ ሥራዎች እየተሰሩ ቢሆንም አዲስ አበባ እንደ  የዓለም አቀፍ ከተማነቷ አርዓያ የሆነ ከዚህ የተሻለ የትምህርት ስርአት በማስከበር አመርቂ ውጤት ማስመዝገብ ይጠበቅባታል ብለዋል ::  አክለዉም  የዛሬው የጋራ መድረክ ከሩብ ዓመት ሥራ አፈፃፀም ባለፈ የቅንጅት ስራዎች ያሉበት ደረጃና በሱፐርቪዥንና ኢንስፔክሽን የተገኙ ውጤቶች የሚገመገሙበት መሆኑን ጠቁመዋል ::

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ  ሀላፊ ተወካይና የቢሮ አማካሪ  አቶ ጥላሁን ፍቃዱ በ2016 ዓ.ም አንደኛ  ሩብ ዓመት ሥራ አፈፃፀማችን የታዩ ጥንካሬዎችን ማስቀጠልና እጥረቶችን መገምገም በቀጣይ የተሻለ የትምህርት ጥራት  ደረጃ ላይ ለመድረስ ያስችላል ብለዋል :: የእቅድ አፈፃፀሙን ከትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ጋር በጋራ መገምገም ደግሞ ለሀገር መፃኢ ዕድል ያለውን ያለውን በጎ አስተዋፅኦ የሚያመላክት ይሆናልም ብለዋል :: አክለውም በሩብ ዓመቱ ያየነው የትምህርት ጥራትና ደረጃ መሻሻል ሳይቀንስ ከዚህ የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ መሰራት ይገባል ብለዋል ::

የትምህርት ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅ  አቶ አድማሱ ደቻሳ በበኩላቸው በሩብ ዓመት የታዩ ውጤቶች የቅንጅት ሥራ ውጤት መሆናቸውን ገልፀው የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ  የመንግስት ትምህርት ቤቶች እውቅና ፈቃድ ለመስጠት የተቀመጡ ቼክሊስቶችን መመልከትና ለምዘና ቅድመ ዝግጅት ማድረግ እንደሚጠበቅ አሳስበዋል ::

በእለቱ ለመንግስት ትምህርት ቤቶች የእውቅና ፈቃድ መስጠት ያስችላል የተባለ ሰነድ ቀርቦ  ውይይት ተደርጎበታል ::

በ 2015 የኢንስፔክሽን ግኝት የተሻለ አፈፃፀም ላሳዩ 3 ትምህርት ቤቶችም ከትምህርት ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን የእውቅና ሰርተፍኬት ተሰጥቷቸዋል ::

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 205
  • 158
  • 7,078
  • 31,331
  • 147,475
  • 147,475