የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2015 በጀት ዓመት ባስመዘገበው የላቀ አፈፃፀም ሽልማት ተበረከተለት ።

by | ዜና

(ጥቅምት 23/2016 ዓ.ም)  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2015 በጀት ዓመት ባስመዘገበው የላቀ አፈፃፀም ከከተማ አስተዳደሩ እውቅና እና ሽልማት ተበርክቶለታል፡፡

ቢሮው  በከተማ አስተዳደሩ ስር ከሚገኙ የካቢኔ አባል ከሆኑ ሴክተር መስሪያ ቤቶች 3ኛ በመውጣቱ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበቤ የመኪና እና የምስጋና የምስክር ወረቀት ተሰጥቶታል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር  በ2015 በጀት ዓመት  የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ ተቋማት በሰጠው እውቅና የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት  ቢሮ እውቅና በማግኘቱ የተስማንን ታላቅ ደስታ እየገለጽን እውቅናው ለድካማችን ካሳ እና ለቀጣይ ስራ መነሳሳትን የሚፈጥር በመሆኑ ለዚህ ውጤት መመዝገብ አስተዋፅዎ ላደረጋችሁ አካላት በሙሉ  ምስጋና እናቀርባለን።

 

እንኳን ደስ አላችሁ!

 

እንኳን ደስ  አለን!

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 205
  • 158
  • 7,078
  • 31,331
  • 147,475
  • 147,475