የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርአተ ትምህርት ማበልጸጊያና ትግበራ ዳይሬክቶሬት በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ስልጠና ሰጠ።

by | ዜና

(ጥቅምት 17/2016 ዓ.ም) ስልጠናው በተጓዳኝ ክበባት አደረጃጀት፤በማስተማሪያ እቅድ አዘገጃጀት እንዲሁም በክፍል ውስጥ የሚደረግ ምልከታን አስመልክቶ በተዘጋጀ ቼክ ሊስት ዙሪያ የተሰጠ ሲሆን በመርሀ ግብሩ በከተማ አስተዳደሩ ከሚገኙ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተመለመሉ መምህራንን ጨምሮ የክፍለ ከተማ የስርአተ ትምህርት ትግበራ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል።

ስልጠናው በዋናነት ከተጓዳኝ ክበባት አደረጃጀት ጋር በተገናኘ በአዲሱ ስርአተ ትምህርት በተካተቱ ጉዳዮች እንዲሁም የስርአተ ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ባለሙያዎች በክፍል ውስጥ ስለሚያደርጉት ምልከታ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ታስቦ  መዘጋጀቱን የቢሮው የሒሳብ ስርአተ ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ባለሙያ አቶ ፍቃዱ ፋንታዬ ገልጸው በትምህርት ቤት በመምህራን ስለሚዘጋጀው የማ ስተማሪያ እቅድ አዘገጃጀት ጋር በተገናኘም ሰልጣኞቹ የሚፈለገውን ግንዛቤ ጨብጠው በቀጣይ በክፍለከተማ ደረጃም ሆነ በየትምህርት ቤቱ ተመሳሳይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን መስጠት እንዲችሉ ታስቦ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል።

በመርሀ ግብሩ የቢሮው የስርአተ ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ባለሙያዎች አቶ ሙሉነህ ተክለብርሀን እና አቶ ጌታሁን ጌታቸው በማስተማሪያ እቅድ አዘገጃጀት ዙሪያ ስልጠና ሲሰጡ በክፍል ውስጥ የሚደረግ ምልከታን በተመለከተ ደግሞ የስርአተ ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ባለሙያ በሆኑት አቶ ተካልኝ ገብረስላሴ እና አቶ በላይ በለጠ የተሰጠ ሲሆን የተጓዳኝ ክበባት አደረጃጀትን የተመለከተ ስልጠና በአቶ ፍቃዱ ፋንታዬ ተሰቶ ተሳታፊዎች ውይይት አካሂደዋል።

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

https://twitter.com/aacaebc

SITE VISITORS

  • 0
  • 178
  • 249
  • 2,414
  • 8,966
  • 243,948
  • 243,948