(ጥቅምት 16/2016 ዓ.ም) ሰራተኞቹ ቢሮው በቅርቡ ባወጣው የስራ ማስታወቂያ ተወዳድረው በማለፍ በጽዳት፣ጥበቃ እና ሞግዚትነት የተቀጠሩ ሲሆን ኦረንቴሽኑ ስራ ከመጀመራቸው በፊት ስለተቋሙ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን በመርሀ ግብሩ ተገልጿል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የህንጻ አስተዳደርና አገልግሎት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አዱኛ ድሪባ በመርሀ ግብሩ ባስተላለፉት መልዕክት ኦረንቴሽኑ ሰራተኞቹ አዲስ እንደመሆናቸው ስለተቋሙ ተልዕኮም ሆነ በስራ ላይ ስለሚጠበቅባቸው ኃላፊነት በአግባቡ ተገንዝበው በስራቸው ውጤታማ እንዲሆኑ ታስቦ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል።
በመርሀ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የለውጥና መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዳዊት ከበደ የስራ ላይ ስነ-ምግባር ምንነትና መርሆችን የተመለከተ ገለጻ አድርገው ተ ሳታፊዎች ውይይት አካሂደዋል።
አዲስ የተቀጠሩ ሰራተኞች የስራ ሰአታቸውን በአግባቡ በማክበርም ሆነ በስራ ገበታ ላይ በመገኘት በተመደቡበት ሞያ ውጤታማ ስራ መስራት እንደሚጠበቅባቸው የቢሮው የሰው ሀብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ተወካይ አቶ ብርሀኑ ክበበው አስገንዝበዋል።
0 Comments