የስርዓተ ትምህርት ማበልፀጊያ እና ትግበራ ዳይሬክቶሬት መሰረታዊ የስራ ሂደት ለውጥ ፣ አዲሱ ስርዓተ ትምህርት ለውጥ እና ተከታታይ ምዘና በሚሉ ሶስት ርዕሰ ጉዳዮች ላይ በሁሉም ክፍለ ከተሞች ለሚገኙ የስርዓተ ትምህርት ቡድን መሪና ባለሙያዎች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል ::
የመሰረታዊ ሥራ ሂደት ለውጡ በሥርዓተ ትምህርት ላይ የነበሩ ክፍተቶች ለመቅረፍ እንደሚያስችል የገለፁት የስርዓተ ትምህርት ማበልፀጊያ እና ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ታለማ ስልጠናው መሰጠቱ የተገልጋይ ፍላጎትን ከማሟላት ባለፈ የለውጥ አስፈላጊነትን የተረዳ ባለሙያ በመፍጠርና ብቁ ዜጋን ማፍራት ያስችላል ብለዋል:: የአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ለውጥን አስመልክቶ የመወያያ ሰነድ ያቀረቡት አቶ ሙሉነህ ተክለብርሃን በበኩላቸው አዲሱን አደረጃጀት መሰረት በማድረግ አዲስ ባለሞያዎች በስራው ላይ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው እንደሚያግዝ ተናግረዋል::
0 Comments