የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቢሮው አጠቃላይ ሰራተኞች በተገኙበት በ2016ዓ.ም 1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ዙሪያ ውይይት አካሄደ።

by | ዜና

(ቀን 9/2/2016 ዓ.ም) በውይይቱ ቢሮው በበጀት አመቱ በ1ኛ ሩብ አመት ባከናወናቸው ተግባራት እንዲሁም የሩብ አመቱ የመልካም አስተዳደር አፈጻጸም አገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ፣የሌብነትና ብልሹ አሰራር መታገያ ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ የቢሮው ሰራተኞች ውይይት አካሂደዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቢሮ ኃላፊ አማካሪ ወይዘሮ አበበች ነጋሽ በውይይቱ ባስተላለፉት መልዕክት ቢሮው በ2016 ዓ.ም 1ኛ ሩብ አመት ባከናወናቸው ተግባራት ዙሪያ የቢሮው ማኔጅመንት እና አጠቃላይ ካውንስል አባላት ቀደም ሲል ውይይት ማካሄዳቸውን ገልጸው የቢሮው ሰራተኞች በሩብ አመቱ በተከናወኑ ተግባራት ዙሪያ ተወያይተው በቀጣይ የተሻለ ስራ መስራት እንዲቻል ታስቦ ውይይቱ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ኡመር በበኩላቸው ቢሮው በ2016 ዓ.ም 1ኛ ሩብ አመት ባከናወናቸው ተግባራት የተለያዩ ውጤቶችን ማስመዝገቡን ጠቁመው ለተገኘው ውጤት የቢሮው ባለሙያዎች አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን በመግለጽ በቀሪ የትግበራ ምዕራፍም ከዚህ በተሻለ ውጤታማ በመሆን የተማሪዎች ውጤትና ስነ-ምግባር ለማሻሻል በጋራ መስራት እንደሚገባ አስረድተዋል።

በውይይቱ የቢሮው የእቅድና በጀት ክትትል ዳይሬክተር አቶ ጌታሁን ለማ የ1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡ ሲሆን ቢሮው በበጀት አመቱ በአራት የትኩረት መስኮች የተቀመጡ እና በ11 ግቦች ስር የሚገኙ 105 አላማዎችን ለማሳካት የተለያዩ ተግባራትን ማከናወኑን አስገንዝበዋል።

የለውጥና መልካም አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ዳዊት ከበደ የሩብ አመቱን የመልካም አስተዳደር እና የብልሹ አሰራር እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበው ውይይት ተካሂዷል።  

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 187
  • 249
  • 2,423
  • 8,975
  • 243,957
  • 243,957