የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት አስተዳደርና መረጃ ስርአት ቡድን ለ2016 ዓ.ም ፈጣን መረጃ ለመሰብሰብ በተዘጋጀ ቼክ ሊስት ዙሪያ ውይይት አካሄደ፡፡

by | ዜና

(ቀን 9/2/2016 ዓ.ም) በውይይቱ ከአስራአንዱ ክፍለከተሞች የተውጣጡ የዘርፉ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን  የውይይቱ ተሳታፊዎች በየክፍለከተማቸው ከፈጣን መረጃ አሰባሰብ ጋር በተገናኘ በተለይም ከተማሪ ቅበላ ጋር አንጻር ያለውን አፈጻጸም ሪፖርት አድርገው ውይይት ተካሂዱዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት አስተዳደርና መረጃ ስርአት ቡድን ተወካይ አቶ አለምነህ መላኩ በውይይቱ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት የትምህርት ሴክተሩ የ2016ዓ.ም ፈጣን መረጃ ጥራቱን በጠበቀ መልኩ ማደራጀት እንዲቻል ከተማሪ ቅበላ ጋር በተገናኘ እስካሁን ያለውን አፈጻጸም በተመለከተ እና በከተማ አስተዳደሩ ያሉ የትምህርት ተቋማት ብዛት መረጃን የያዘ ቼክሊስት መዘጋጀቱን ገልጸው በተጨማሪም በቼክሊስቱ ወደሸገር ሲቲም ሆነ ወደ አዲስ አበባ የገቡ ትምህርት ቤቶችን የተመለከተ መጠይቅ መካተቱን በመጥቀስ ክፍለከተሞችም መረጃዎችን በቼክሊስቱ መሰረት በማደረጃት በተቀመጠው የጊዜ ገደብ መሰረት ለቢሮው ሪፖርት ማድረግ እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል፡፡

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 1
  • 187
  • 249
  • 2,423
  • 8,975
  • 243,957
  • 243,957