የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ካውንስል አባላት የ2016 ዓ.ም 1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸምን ገመገሙ።

by | ዜና

(ቀን 8/2/2016 ዓ.ም) በውይይቱ ቢሮው በበጀት አመቱ በ1ኛ ሩብ አመት ያከናወናቸው ተግባራት እንዲሁም የሩብ አመቱ የመልካም አስተዳደር አፈጻጸም አገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ፣የሌብነትና ብልሹ አሰራር መታገያ ዕቅድ አፈጻጸምና የሱፕርቪዥን ግኝት ሪፖርት  ቀርቦ የካውንስሉ አባላት ውይይት አካሂደዋል።

   

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቢሮ ኃላፊ አማካሪ ወይዘሮ አበበች ነጋሽ በውይይቱ ባስተላለፉት መልዕክት ቢሮው በ2016 ዓ.ም 1ኛ ሩብ አመት ባከናወናቸው ተግባራት ዙሪያ የቢሮው ማኔጅመንት ቀደም ብሎ ውይይት ማካሄዱን ገልጸው የአጠቃላይ ካውንስል አባላቱ በሩብ አመቱ በተከናወኑ ተግባራት ዙሪያ በሚያካሂዱት ውይይት የሚያነሷቸው ሀሳቦች ተካተው ከቢሮው ጠቅላላ ሰራተ ኞች ጋር ተመሳሳይ ውይይት እንደሚካሄድም አስታውቀዋል።

      

በውይይቱ የቢሮው የእቅድና በጀት ክትትልና ግምገማ  ዳይሬክተር አቶ ጌታሁን ለማ የ1ኛ ሩብ አመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ፣ የለውጥና መልካም አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ዳዊት ከበደ የመልካም አስተዳደር እና የብልሹ አሰራር መታገያ እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት እንዲሁም የአጠቃላይ ትምህርት ሱፐርቪዥን ዳይሬክተር አቶ ፀጋዬ አሰፋ በሩብ አመቱ በትምህርት ተቋማት የተካሄደ የሱፐርቪዥን ግኝት ሪፖርት አቅርበው  ውይይት ተካሂዷል።

           

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 183
  • 249
  • 2,419
  • 8,971
  • 243,953
  • 243,953