የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሰንደቅ ዓላማ ቀንን አከበረ።

by | ዜና

(አዲስ አበባ 5/2/2016 ዓ.ም)  የዘንድሮው የሰንደቅ አላማ ቀን ለ16 ጊዜ የተከበረ ሲሆን እለቱም “የሰንደቅ ዓላማችን ከፍታ ለሕብረ-ብሔራዊ አንድነታችንና ለሉዓላዊነታችን ዋስትና ነው!” በሚል መሪ ቃል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ እና የአዲስ አበባ ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች በተገኙበት ተከብሩዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ኡመር በመርሀ ግብሩ ባስተላለፉት መልዕክት የሰንደቅ ዓላማ ቀን መከበር ለሕብረ-ብሔራዊ አንድነት እና ለሉዓላዊነት መጠናከር ትልቅ ትርጉም እንደሚኖረው ጠቁመው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትም የሰንደቅ ዓላማ ቀን እንዲከበር ሲወስን ለሃገር ክብር እና ጥቅም ሁላችንም የበኩላችንን ለመወጣት በሰንደቅ ዓላማ ፊት ዳግም ቃላችንን የምናድስበት እንዲሆን ለማስቻል መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡

በዓሉ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ፣ በመንግስት ተቋማት፣ በክልሎች እና በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች ፣ በመከላከያ ሠራዊት ካምፖች እንዲሁም በኤምባሲዎች እና የኢትዮጵያ ሚሲዮኖች በተመሳሳይ ሰዓት ከረፋዱ 4፡30 ላይ በደማቅ ሁኔታ እንደሚከበር ቀደም ሲል በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መገለጹ ይታወቃል።  

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 178
  • 249
  • 2,414
  • 8,966
  • 243,948
  • 243,948