የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስነምግባርና ፀረሙስና ዳይሬክቶሬት ለቢሮው አጠቃላይ ሰራተኞች በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠቱን አስታወቀ።

by | ዜና

(መስከረም 19/2016 ዓ.ም) ስልጠናው በዋናነት  በቅርቡ በቢሮ ደረጃ የሚካሄደውን የሰራተኞች ሀብት ምዝገባና አስቸኩዋይ ሙስናን የመከላከል ተግባርን መሰረት አድርጎ የተሰጠ ሲሆን የቢሮው ሰራተኞችም በጉዳዩ ዙሪያ በቂ ግንዛቤ በመያዝ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ የሚያስችል ስልጠና መሆኑን የቢሮው የስነምግባርና ፀረሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አስራት ሽፈራው አስታውቀዋል።

ዳይሬክተሩ አክለውም ሀብት የማስመዝገብ ተግባር ግልጽነትን ለመፍጠር ታስቦ የሚካሄድ እንደመሆኑ ሰራተኛው በስሙ የሚገኘውን ሀብት በቅንነትና ታማኝነት ማስመዝገብ እንደሚጠበቅበት ጠቁመው አስቸኩዋይ ሙስናን ከመከላከል አንጻርም ባለሙያው ከስራ ክፍሉ ጋር በመተባበር ብልሹ አ ሰራርን መታገል እንደሚገባው አስገንዝበዋል።

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 205
  • 158
  • 7,078
  • 31,331
  • 147,475
  • 147,475