(አዲስ አበባ 11/1/2016 ዓ.ም) ውይይቱ በዋናነት በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተካሄደ ሱፐርቪዥንን መሰረት አድርጎ የተካሄደ ሲሆን በሱፐርቪዝኑ የተገኙ ግብረመልሶች በቢሮው የቀዳማይ ልጅነት እንክብካቤ ባለሙያ ወይዘሮ ፍሬሕይወት በቀለ አማካይነት ቀርቦ ውይይት ተካሂዱዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ታጋይቱ አባቡ በውይይቱ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ለቀጣዩ የትምህርት እርከን መሰረት የሚጣልበት እንደመሆኑ ህጻናቱ ለደረጃው የተዘጋጀውን የትምህርት አገልግሎት ማግኘት እንዲችሉ ቢሮው በርካታ ተግባራትን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ገልጸው በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ 220 የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተደረገ ሱፐርቪዝን ግብረመልስን መሰረት አድረጎ ዛሬ የሚካሄደው ውይይት ትምህርት ቤቶች ልምድ እንዲለዋወጡ የሚያስችላቸው መሆኑን አስረድተዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ጉዳዮች ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወይዘሮ በላይነሽ ይሻው በበኩላቸው በቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተካሄደው ሱፐርቪዝን ትምህርት ቤቶቹ ለ2016ዓ.ም የትምህርት ዘመን ያደረጉት ቅድመ ዝግጅት ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኝና በግብረመልሱ የተቀመጡ ግኝቶችን መሰረት በማድረግ የተስተዋሉ ክፍተቶችን በመቅረፍ ወደ መማር ማስተማር ስራው ለመግባት እንደሚረዳ አስታውቀዋል፡፡
0 Comments