የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ “ቅንጅታዊና የትብብር አሰራር ለላቀ ውጤት!” በሚል መሪ ቃል በጋራ የተለያዩ ተግባራት ከሚያከናውኑ ተቋማት ጋር የትስስር ፊርማ ተፈራረመ።

by | ዜና

(አዲስ አበባ 10/1/2016 ዓ.ም) በስምንምነት ሰነድ ፊርማ መርሀ ግብሩ ቢሮው በ2016 ዓ.ም አብረውት የተለያዩ ተግባራትን ከሚያከናውኑ ተቋማትና አደረጃጀቶች ጋር ከመፈራረሙ ባሻገር በ2015ዓ.ም በትስስር ፊርማው መሰረት ውጤታማ ስራ  ለሰሩ ተቋማት እውቅና ሰቷል።

የትምህርት ስራ ትውልድ የሚቀረጽበትና የነገ ሀገር ተረካቢ ዜጎች የሚታነጹበት ተግባር እንደመሆኑ ተልዕኮው የሚፈለገውን ውጤት ማስመዝገብ እንዲችል የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ እና የቢሮ ኃላፊ ተወካይ አቶ ወንድሙ ኡመር ገልጸው በ2016ዓ.ም የትምህርት ዘመን በትስስር ፊርማው መሰረት ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር የተማሪዎችን ውጤትና ስነምግባር ለማሻሻል በጋራ እንደሚሰራና አፈጻጸሙንም የመገምገም ተግባር እንደሚከናወን አስገንዝበዋል።

የቢሮ ኃላፊ አማካሪ ወይዘሮ አበበች ነጋሽ በበኩላቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2015ዓ.ም የትምህርት ልማት ስራውን ውጤታማ ለማድረግ ከተለያዩ ተቋማት ጋር ባከናወናቸው የተለያዩ ተግባራት አበረታች ውጤት ማስመዝገቡን ጠቁመው ከተቋማቱ ጋር ከመፈራረም ባሻገር በየሩብ አመቱ የተከናወኑ ተግባራትን የመገምገም ተግባር ሲያከናውን መቆየቱን ገልጸዋል።

በመርሀ ግብሩ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ በ2015ዓ.ም ከተለያዩ ተቋማት ጋር በጋራ ያከናወናቸው ተግባራት ሪፖርት በቢሮው የለውጥና መልካም አስተዳደር ዳይሬክተር በአቶ ዳዊት ከበደ ቀርቦ ውይይት የተካሄደ ሲሆን ተቋማቱም በ2016ዓ.ም ቀደም ሲል ከነበረው በተሻለ በትስስሩ መሰረት የተቀመጠላቸውን ተግባር ለማከናውን ዝግጁ መሆናቸውን አስታውቀዋል።

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 205
  • 158
  • 7,078
  • 31,331
  • 147,475
  • 147,475