የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ የ 8ኛ ክፍል  ፈተና ሰኔ 19 እና 20 እንዲሁም የ 6ኛ ክፍል ፈተና ሰኔ 26 እና 27 እንደሚሰጥ ተናግረዋል::

አያይዘውም ቢሮው ከተማ አቀፍ ፈተናዎቹን ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመስጠት ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን የተናገሩ ሲሆን ትምህርት ቤቶች ተማሪዎቹን የበለጠ ማዘጋጀት እንዲችሉ ከከተማና ክፍለ ከተሞች ጋር በጋራ በመሆን የሞዴል ፈተናዎችን እንዲሰጡ አሳስበዋል ::

በ 2015 ዓ. ም 75,100 የ8ኛ እንዲሁም 75,078 የ 6ኛ ክፍል ተማሪዎች ከተማ አቀፍ ፈተናውን እንደሚወስዱ ከስራ ክፍሉ ያገኘነው መረጃ ያሳያል ::