የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሰራተኞች በመስከረም ወር በሚከበሩ የአደባባይ በአላት አከባበር ዙሪያ ውይይት አካሄዱ።

by | ዜና

(አዲስ አበባ 8/1/2016 ዓ.ም)  ውይይቱ በዋናነት በቅርቡ የሚከበሩት የመስቀል ደመራ እና የኢሬቻ ክብረ በአላት ያለምንም የጸጥታም ሆነ ሌሎች ስጋቶች እንዲከበሩ የቢሮው ሰራተኞች የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ ታስቦ የተዘጋጀ መርሀ-ግብር ነው።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አሊ ከማል ውይይቱ በዋናነት በከተማችን በመስከረም ወር የሚከበሩት የመስቀል ደመራም ሆነ የኢሬቻ ክብረ በአላት ስርዓታቸው ተጠብቆ እንዲከበር የቢሮው ሰራተኞች የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት እንዲወጡ ታስቦ መዘጋጀቱን ገልጸው ክብረ በአላቱ በዩኔስኮ የማይዳሰሱ ቅርስ ሆነው የተመዘገቡ እንደመሆናቸው በበአላቱ ለመታደም የሚመጡ በርካታ የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ ዜጎች በአላቱን ያለምንም ስጋት እንዲያከብሩ ከወዲሁ የቅድመ ዝግጅት ስራ እየተሰራ እንደሚገኝም አስታውቀዋል።

የመስቀል ደመራ በአል ሀይማኖታዊ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ እንዲሁም የገዳ ስርዓት መገለጫ የሆነው የኢሬቻ በአል ሰላማዊ በሆነና ትውፊቱን ጠብቀው በድምቀት እንዲከበሩበከተማ አስተዳደሩ የተለያዩ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙ የቢሮ ኃላፊ የቴክኒክ አማካሪ አቶ ዳኛቸው ከበደ ከመስቀል ደመራ እና ከኢሬቻ በአላት አከባበር ጋር በተገናኘ የተዘጋጀ የመወያያ ሰነድ ባቀረቡበት ወቅት ገልጸዋል።

 

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 30
  • 222
  • 1,584
  • 6,364
  • 214,625
  • 214,625