የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ትግበራ ዳይሬክቶሬት የቅድመ አንደኛ ትምህርት ጀማሪ ተማሪዎችን የተመለከተ ስልጠና ሰጠ ::

by | ዜና

አዲስ አበባ ነሀሴ 27/2015 ዓ.ም  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የዘርፈ ብዙና ቀዳማይ ልጅነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ /ሮ  በላይነሽ የሻው በስልጠናው መክፈቻ ባደረጉት ንግግር በከተማችን የሚገኙ እድሜያቸው ለትምህርት የደረሰ ተማሪዎች በወቅቱ ምዝገባ እንዲያካሂዱ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ ለሰልጣኞች ተናግረዋል ::

በቅድመ አንደኛ ትምህርት ያለፈ ተማሪ የትምህርት አቀባበል የቅድመ አንደኛ ካልተማረ ሰፊ ልዩነት አለው ያሉት ዳይሬክተራ የምዝገባ ወቅት ሳያልፍ በመስሪያ ቤታችንና በመኖሪያ አካባቢያችን ያሉ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ተቋማት እንዲመጡ ሁላችንም ቅስቀሳ  ማድረግ አለብን ሲሉ አሳስበዋል::

አያይዘውም ተማሪዎች ወደትምህርት እንዲመጡ ከማድረግ ባለፈ የትምህርት ተቋማትን ለመማር ማስተማር ምቹ ለማድረግ በትምህርት ቤቶች አካባቢ ያሉ አዋኪ ጉዳዮችን ለመከላከል በትምህርት ተቋማት ያሉ ባለሙያዎች ኃላፊነት ትልቁን ድርሻ ይይዛል ብለዋል ::

ከቅን ልቦና በጎ አድራጎት ድርጅት የመጡት አቶ እሱባለው ደበሽ ሰልጣኞች አንድም እድሜው ለትምህርት የደረሰ ሕፃን ያለትምህርት እንዳይቀር ለትውልድ እገዛ እንዲያደርጉ አሳስበዋል ::

በስልጠናው የቢሮው አጠቃላይ ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል ::

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 311
  • 374
  • 4,292
  • 15,622
  • 98,488
  • 98,488