አዲስ አበባ ነሀሴ 24 /2015 ዓ.ም በስልጠናው የክፍለ ከተማ የልዩፍላጎትና የጎልማሶች ትምህርት ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን በዛሬው መርሀ ግብር የ2016 ዓ.ም የልዩ ፍላጎት/አካቶ ትምህርት አበይት ተግባራት ትውውቅና የትምህርት ስርአቱ ማዕቀፎች በቢሮው የልዩ ፍላጎት/አካቶ ትምህርት ባለሙያ በአቶ ፀጋዬ ሁንዴ ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።
ውይይቱ በዋናነት በቅርቡ በከተማ ደረጃ በተካሄደው የትምህርት ጉባኤ የቀረበውን የልዩ ፍላጎት/አካቶ ትምህርት የንቅናቄ ሰነድ መሰረት አድርጎ ለክፍለ ከተማ የዘርፉ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች ግንዛቤ ለመፍጠር ታስቦ መዘጋጀቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የልዩ ፍላጎትና የጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል አስራት ገልጸው በዘርፉ የተጀመረው ተግባር ውጤታማ እንዲሆን በየደረጃው የንቅናቄ ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስገንዝበዋል።
አቶ ዳንኤል አክለውም የልዩ ፍላጎትም /አካቶ ትምህርት አገልግሎትን ውጤታማ ለማድረግ በትምህርት ቤቶች የድጋፍ መስጫ ማእከላት መቃቃማቸውን ጠቁመው በክፍለ ከተማ የሚገኙ የዘርፉ ባለሙያዎች በየደረጃው የሚገኙ መዋቅሮቻቸውን በማስተባበር በተለያዩ ችግሮች ምክንያት የትምህርት እድል ያላገኙ ዜጎች ወደትምህርት ገበታ እንዲመጡ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።
0 Comments