የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ሁለንተናዊ ርብርብ ለትምህርት ተቋማት በሚል መሪ ቃል 30ኛውን የትምህርት ጉባኤ ማካሄድ ጀመረ።

by | ዜና

አዲስ አበባ ነሀሴ 18/2015 ዓ.ም  በጉባኤው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክብርት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ፣የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ፣የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ ካቢኔ አባላት፣በየደረጃው የሚገኙ የትምህርት አመራሮች፣ መምህራን ፣ተማሪዎችና ወላጆች ተሳታፊ ሆነዋል።

      

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ክብርት ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በጉባኤው መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት ከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ በጀት በመመደብና የተለያዩ የትምህርት ቁሳቁሶችን በማቅረብ የትምህርት ሴክተሩን በመደገፍ ላይ እንደሚገኝ ገልጸው የትምህርት ጥራትን የማረጋገጥ ሂደቱ የሚፈለገውን ውጤት ማስመዝገብ እንዲችል የትምህርት ቤቶችን መሰረተ ልማት በማሻሻል ደረጃቸውን ከፍ ማድረግ እንደሚገባ በመጥቀስ ከተማ አስተዳደሩም የሚጠበቅበትን ኃላፊነት እንደሚወጣ አስገዝበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በበኩላቸው የዘንድሮው ጉባኤ ከ28 አመት በኋላ የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በተሰጠበትና የ8ኛ ክፍል ውጤትም ላለፉት አመታት ቀጣይነት ባለው መልኩ መሻሻልን ባሳየበት አመት የሚካሄድ መሆኑ ለየት እንደሚያደርገው ጠቁመው አዲሱን ስርአተ ትምህርት በአግባቡ ተግባራዊ ለማድረግ የከተማውን አውድ መሰረት ያደረገ የመማሪያ መጽሀፍ ተዘጋጅቶ ወደ ተግባር መገባቱን  በመጥቀስ ጉባኤው የነበሩ ጠንካራ ጎኖችንም ሆነ የታዩ ጉድለቶችን መነሻ በማድረግ ከፍተ ኛ ውይይት የሚካሄድበትና ቀጣይ አቅጣጫ የሚቀመጥበት መሆኑንም ትምህርት ማህበረሰቡን ወደተሻለ ደረጃ የሚያሸጋግርና የአንድ ሀገር የሞራል እሴት መለኪያ መሆኑን የኢፌድሪ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ በመርሀ ግብሩ ገልጸው ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የትምህርት ፍትሀዊነትንም ሆነ ጥራትን ለማረጋገጥ የተቋማቱን ደረጃ የማሻሻል እና መምህራንን የማሰልጠን ተግባሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስረድተዋል።

በጉባኤው የአዲስ አበባ መምህራን ማህበር እና የአዲስ አበባ የተማሪ ወላጅ ማህበር የ2015ዓ.ም ሪፖርትና በቀጣይ የሚያከናውኑዋቸው ተግባራት በሰብሳቢዎቻቸው የቀረበ ሲሆን የቢሮው የ2015 እቅድ አፈጻጸም ሪፖርትና የ2016ዓ.ም መሪ እቅድ ለጉባኤተኛው ቀርቦ ውይይት እንደሚካሄድም ከወጣው መርሀ ግብር ለማወቅ ተችሏል።

     

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 315
  • 374
  • 4,296
  • 15,626
  • 98,492
  • 98,492