የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የለውጥና መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በቢሮው ለሚገኙ ለዳይሬክቶሬቶችና ቡድኖች ምዘና አደረገ::

by | ዜና

(አዲስ አበባ ነሀሴ 16/2015 ዓ.ም)  የለውጥና መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዳዊት ከበደ በዕለቱ ለመዛኞች ባደረጉት ገለፃ ላይ እንዳሉት በምዘናው የመልካም አስተዳደርና ሪፎርም ስራዎች እንደሚገመገሙ ተናግረዋል:: አያይዘውም እቅድና ሪፖርት እንዲሁም የስራ አፈፃፀምና አገልግሎት አሰጣጥ  ላይ ትኩረት አድርጎ በበጀት ዓመቱ የተከናወኑ መልካም አፈፃፀሞችን ለማበረታታት የታዩ ክፍተቶችንም ቀጣይ በማስተካከል ወደፊት ለመምጣት እንደሚያስችል አብራርተዋል ::

አቶ ዳዊት እንዳሉት የምዘና ውጤቱ በሥራ ክፍሎች መካከል ተወዳዳሪነት በመፍጠር የተሻለ የስራ አቅም ለመፍጠር ያበረታታል ብለዋል ::

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 0
  • 175
  • 2,114
  • 9,135
  • 234,185
  • 234,185