የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አጠቃላይ ትምህርት ሱፐርቪዥን ዳይሬክቶሬት የ 2015 ዓ.ም እቅድ አፈፃፀም ግምገማና የ 2016 ዓ.ም እቅድ ላይ ውይይት አካሄደ ::

by | ዜና

(አዲስ አበባ ነሐሴ 12/2015 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አጠቃላይ ትምህርት ሱፐርቪዥን ዳይሬክቶሬት የ2015 ዓ. ም እቅድ አፈፃፀም ግምገማና የ 2016 ዓ. ም እቅድ ላይ ውይይት  ያካሄደ ሲሆን በመድረኩ የ2016 የትምህርት ዘመንን  እቅድ ለማቀድ ነባራዊ ሁኔታውን በመቃኝት የነበሩ እጥረቶችን መለየትና በተለዩ ችግሮች ላይ መግባባት ዋናው ነው ያሉት   የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አሊ ከማል በሚቀርበው እቅድ ላይ ገንቢ አስተያየት በመስጠትና በመወያየት የበጀት ዓመቱን ተግባራት በስኬት ለማጠናቀቅ ሁሉም ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርግ አደራ ብለዋል::

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አጠቃላይ ትምህርት ሱፐርቪዥን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፀጋዬ አሰፋ  የውይይት መድረኩ የ2015 ዓ. ም እቅድ አፈፃፀም ምን እንደሚመስል በግልፅ የሚያሳይ ይሆናል በማለት የታዩ ችግሮችን ለመለየትና እንዴት መፍታት እንዳለብን የምንወያይበትና በቀጣይ የትምህርት ዘመን የተሻለ ሥራ ለመስራት አዲሱን እቅዳችንን የምናቅድበት ይሆናል ሲሉ ተናግረዋል:: አቶ ፀጋዬ አያይዘውም ተሳታፊዎች በሚነሱ ዋናዋና ጉዳዮች ላይ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ እቅዱን እንዲያዳብሩ ይጠበቃል ብለዋል ::

በውይይቱ የሁሉም ክፍለ ከተማ 1ኛና 2ኛ ደረጃ ክላስተር አስተባባሪዎች፣  የክፍለ ከተማ አስተባባሪዎች እና የቢሮ ሱፐርቫይዘሮች እንደሚሳተፉ ከስራ ክፍሉ ያገኘነው መረጃ ያሳያል ::

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 28
  • 222
  • 1,582
  • 6,362
  • 214,623
  • 214,623