የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የህንጻ አስተዳደርና ጥገና አገልግሎት ጽህፈት ቤት ለጽህፈት ቤቱ ሰራተኞች ለሁለት ቀን የሚቆይ ስልጠና በመስጠት ላይ መሆኑን አስታወቀ፡፡

by | ዜና

(ነሀሴ 5/2015 ዓ.ም) ስልጠናው በጽህፈትቤቱ በ2015 ዓ.ም የተከናወኑትንም ሆነ በ2016 ዓ.ም የሚከናወኑ ተግባራታን መሰረት አድርጎ ከመሰጠቱ ባሻገር በባለጉዳይ መስተንግዶና በመንግስት ሀብት አጠቃቀም ዙሪያም ስልጠናው እንደሚሰጥ ከጽህፈትቤቱ የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቢሮ ኃላፊ አማካሪ ወይዘሮ አበበች ነጋሽ በስልጠናው መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት በህንጻ አስተዳደር ጽህፈት ቤት ስር የሚገኙ ሰራተኞች ቢሮው የሚያከናውናቸው ተግባራት ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ገልጸው የጽህፈት ቤቱ ሰራተኞች በ2015ዓ.ም በዘርፉ የነበሩ ጠንካራ አፈጻጸሞችንም ሆነ ያጋጠሙ ችግሮችን መሰረት በማድረግ በቀጣዩ አመት የተቀላጠፈ አገልግሎት መስጠት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የህንጻ አስተዳደርና ጥገና አገልግሎት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አዱኛ ድሪባ በበኩላችው ጽህፈትቤቱ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ እና የኮንስትራክሽንና ዲዛይን ቢሮ የሚጠቀሙትን ህንጻ የሚያስተዳድር እንደመሆኑ የተቃማቱን ደህንነት የማስጠበቅና ምድረግቢውን ለአገልግሎት ምቹ የማድረግ ስራ እንደሚሰራ ጠቁመው በ2016ዓ.ም በጽህፈትቤቱ የተቀመጡ ግቦች በአግባቡ ተግባራዊ እንዲሆኑ ተገቢው የድጋፍና ክትትል ስራ እንደሚሰራ አስታውቀዋል፡፡

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 27
  • 222
  • 1,581
  • 6,361
  • 214,622
  • 214,622