የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ 2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን እቅድ አፈፃፀም እና የ 2016 በጀት ዓመት እቅድ ዙሪያ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ውይይት ማካሄድ ጀመረ ::

by | ዜና

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 4 ፣2015 ዓ.ም (ትምህርት ቢሮ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አሊ ከማል በውይይቱ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት የትምህርት ግብ በመልካም ስነ-ምግባር የታነፁና በራስ መተማመን ያለው ትውልድ ማፍራት ሲሆን  ይህን ግብ ስኬታማ ለማድረግም በእቅድ መመራት ዋናው ነው ያሉ ሲሆን የእቅዱን አፈፃፀም መገምገምም ጥንካሬዎችን ለማሳደግና ችግሮችንም ለማረም ይረዳል ብለዋል::

አቶ አሊ አያይዘውም በከተማ አስተዳደሩ በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ የተሰሩ በርካታ ስራዎች መኖራቸውን ጠቁመው ከረጅም አመታት በኃላ የተጀመረውን የ 6ኛ ክፍል እንዲሁም የ 8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናዎች የተመዘገበው ውጤት ለዚህ ማሳያ ይሆናል ብለዋል ::

በእለቱ የ 2015 በጀት ዓመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በእቅድና በጀት ግምገማና ክትትል ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታሁን ለማ የቀረበ ሲሆን በሪፖርቱ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ ሰፊ ሥራ መሰራቱ ተጠቁሟል ::አቶ ጌታሁን በሪፖርታቸው የሴት ተማሪዎች ቁጥር ለማሳደግ :በቴክኖሎጂ የተደገፈ ትምህርት ለማስፋፋትና የልዩ ፍላጎት ትምህርትን ለማሳደግ የተሰሩ በርካታ ስራዎች መኖራቸውን አብራርተዋል ::

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ  ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በዚህ በጀት ዓመት የተሰሩ አበረታችና ወኔ የሚሰጡ ስራዎች መሰራታቸውን አንስተው አዲሱን የትምህርት ፖሊሲ ለመፈፀም የወረደውን አቅጣጫ አመራሩ በአግባቡ መተግበር መቻሉ ለስኬታችን መሰረት ነው ብለዋል ::

በመርሀ ግብሩ በከተማ አስተዳደሩ ከሚገ ኙ የትምህርት አመራሮች ከየትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ዋና እና ምክትል ርዕሳነ መምህራንን ጨምሮ ሱፐርቫይዘሮችና የትምህርት ጽህፈት ቤት አመራሮችና በየደረጃዉ የሚገኙ ባለለሙያዎች በውይይቱ የሚሳተፉ ሲሆን  ተሳታፊዎች ለመወያያነት በተዘጋጁ ሰነዶች ዙሪያ በቡድን በመሆን ሰፊ ውይይት እንደሚያካሂዱ ይጠበቃል ::

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 311
  • 374
  • 4,292
  • 15,622
  • 98,488
  • 98,488