የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርዓተ ጾታ ማስረጽና ማካተት ዳይሬክቶሬት ማህበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም የሚከሰቱ ጾታዊ ጥቃቶችን ለመከላል የሚያስችል ስልጠና ሰጠ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርአተ ጾታ ማስረጽና ማካተት ዳይሬክቶሬት ከUnicef ጋር በመተባበር ማህበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም የሚከሰቱ ጾታዊ ጥቃቶችን ለመከላል የሚያስችል ስልጠና ሰጥቷል፡፡

በስልጠናው የመድኃኒዓለም አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የአይሲቲና እንግሊዘኛ ቋንቋ መምህራን የተሳተፉ ሲሆን ስልጠናውን መውሰዳቸው መምህራኑ በማህበራዊ ሚዲያዎች የሚደርሱ ጾታዊ ጥቃቶችን ለመከላከል የተማሪዎች የራሳቸውን በጎ ተፅእኖ ማሳደር እንዲችሉ ያስችላል ተብሏል ። በስልጠናው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርዓተ ጾታ ማስረጽና ማካተት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ወ/ሮ አበባ ዘውዴ እንዳሉት ስልጠናው ተማሪዎች በተለይም ሴቶች በማህበራዊ ሚዲያዎች በመጠቀም የሚደርሱ ፆታዊ ጥቃቶችን ለመከላከል መምህራን እገዛ እንዲያደርጉ ያስችላል ብለዋል::

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 187
  • 249
  • 2,423
  • 8,975
  • 243,957
  • 243,957