አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 3 ፣2015 ዓ.ም (ትምህርት ቢሮ) በውይይቱ የክፍለ ከተማ የአፋን ኦሮሞ አጠቃላይ ትምህርት ሱፐርቫይዘሮችና አስተባባሪዎች የተሳተፉ ሲሆን በመርሀ ግብሩ የዘርፉ የ2015 ዓ.ም አፈጻጸምና የ2016 ዓ.ም እቅድ ውይይት ተካሂዷል።
ውይይቱ በ2015 የትምህርት ዘመን በአፋን ኦሮሞ አጠቃላይ ትምህርት ዘርፍ የተከናወኑ ጠንካራ ጎኖችን እና በሂደት የታዩ ክፍተቶችን መሰረት በማድረግ መካሄዱን እና በቀጣዩ የትምህርት ዘመን የትምህርት አገልግሎቱን ተደራሽነትም ሆነ ጥራት ለማሻሻል በየደረጃው የሚገኙ ሱፐርቫይዘሮች ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ታስቦ መዘጋጀቱን የቢሮው የአፋን ኦሮሞ አጠቃላይ ትምህርት ሱፐርቪዥን ቡድን መሪ አቶ መንግስቱ አበበ አስታውቀዋል።
ቡድን መሪው አክለውም በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በየደረጃው የሚገኙ የአፋን ኦሮሞ አጠቃላይ ትምህርት ሱፐር ቫይዘሮች የመማር ማስተማር ስራው ውጤታማ እንዲሆን የተለያዩ የድጋፍና ክትትል ስራዎችን ሲሰሩ መቆየታቸውን ጠቁመው በቀጣዩ የትምህርት አመትም የትምህርት ልማት ስራው የሚፈለገውን ውጤት ማስመዝገብ እንዲችል ከተማሪ ቅበላ ጀምሮ በክፍል ውስጥ በመገ ኘት ተገቢውን የድጋፍና ክትትል ስራ መስራት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል።
0 Comments