ቀን 20/8/2014 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የረመዳን ጾምን ሞክንያት በማድረግ የአፍጥር መርሀ-ግብር አከናወነ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በዛሬው እለት ባከናወነው  የአፍጥር መርሀ-ግብር  የቢሮ ሀላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ ፣ የቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊዎች ፣ የቢሮ ሀላፊ አማካሪዎች ፣ የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽፈት ቤት ሀላፊዎች ፣ የእስልምና እምነት ተከታይ የሆኑ እና በመዋቅሩ የሚገኙ የትምህርት ባለሙያዎች እና ሱፐርቫይዘሮች ተሳታፊ ሆነዋል።

በአፍጥር መርሀ-ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ ባስተላለፉት መልዕክት ቢሮው የረመዳን ጾምን ሞክንያት በማድረግ የሚያከናውነው የአፍጥር መርሀ-ግብር የቢሮው ባህል ሆኖ የሚቀጥል ይሆናል ብለዋል።

የአዲስ አበባ ሞክር ቤት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወ/ሮ ዘይነባ ሽኩር በበኩላቸዉ የመረዳዳት እና የመስጠት ባህላችንን አጠናክረን ልንቀጥል ይገባል ብለዋል።