የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ከቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ አሊ ከማል እና ከለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ከአቶ ሲሳይ ኬኔ ጋር በመሆን በዛሬው እለት የተጀመረውን የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና አሰጣጥን በክፍለከተማው በሚገኙ የተለያዩ የመፈተኛ ጣቢያዎች ተዘዋውረው ተመለከቱ።

by | ዜና

ዶክተር ዘላለም ምልከታውን ባካሄዱባቸው ሁሉም የመፈተኛ ጣቢያዎች የጸጥታ አካላትን ጨምሮ የፈተና አስፈጻሚዎች ፈተናው ያለምንም እንከን እንዲካሄድ እያበረከቱ ላለው አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበው ፈተናው ዛሬን ጨምሮ ለቀጣይ ሶስት ቀናት የሚሰጥ እንደመሆኑ የፈተና አስፈጻሚዎችን ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻ አካል ኃላፊነቱን በአግባቡ እንዲወጣ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዘንድሮ በ182 የፈተና ጣቢያዎች 75,090 ተማሪዎች የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ለመውሰድ መመዝገባቸውን ቀደም ሲል መገለጹ ይታወቃል።

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 1
  • 315
  • 374
  • 4,296
  • 15,626
  • 98,492
  • 98,492