የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር 36ኛ መደበኛ የምክር ቤት ጉባኤውን አጠናቀቀ።

by | ዜና

(ቀን ታህሳስ 21/2016 ዓ.ም) ሁለት ቀናትን ቆይታ ባደረገው ጉባኤ ማጠቃለያ መድረክ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ አሊ ከማል ፣ ከከተማ ጀምሮ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ ያሉ የምክር ቤት አባላትና ሌሎች ከማህበሩ ጋር በጋራ የሚሰሩ ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ፕሬዘዳንት አቶ ድንቃለም ቶሎሳ የሙያ ማህበሩ የመምህርነት ሙያ ተገቢውን ክብር እንዲያገኝም ሆነ የመምህራን ጥቅማጥቅም እንዲጠበቅ ከሚያከናውናቸው ተግባራት በተጨማሪ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በሚከናወኑ የተለያዩ ተግባራት የበኩሉን አስተዋጽኦ በማበርከት ላይ እንደሚገኝ ገልጸው በጉባኤው ማጠቃለያ ላይ የተጓደሉ አባላት ምርጫ የተካሄደ መሆኑን ገልፀዋል።

አቶ ድንቃለም አክለውም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ለማህበሩ መጠናከር እያበረከተ ላለው አስተዋፅዎ ማህበሩ የምስጋና ሰርተፌኬት መስጠቱን ገልፀዋል።

የመምህራንን ጥቅማጥቅምች አስመልክቶ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱና የቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ አሊ ከማል ምላሽ ሰጥተዋል።

ጉባኤው በሁለት ቀን ቆይታው የተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ውይይት በማካሄድ ቀጣይ አቅጣጫ ያስቀመጠ ሲሆን ጉባኤተኛው የተስማማበትና የተለያዩ ነጥቦችን ያካተተ የአቋም መግለጫ በማውጣት ተጠናቋል።

 

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 30
  • 222
  • 1,584
  • 6,364
  • 214,625
  • 214,625