አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 3 ፣2015 ዓ.ም (ትምህርት ቢሮ) የትምህርት ጥራትን ለማሻሻልና ብቁ ትውልድ ለመፍጠር የሚደረገውን ጥረት ማገዝ አላማው ማድረጉን ያብራሩት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ መምህራን ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ በላይ ነጋሽ መምህራን ከስልጠናው በዋናነት በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ለ7ኛና 8ኛ ክፍል የሚሰጠውን አጠቃላይ ሳይንስ ትምህርት በማዋሃድ ለማስተማር እና በአይሲቲ ትምህርት አሰጣጥ መሰረታዊ ፅንሰ ሃሳቦችን ማስጨበጥ የሚያስችል ስነ-ዘዴ ለማግኘት እንደሚችሉ አብራርተዋል ::
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አይሲቲ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደረጀ በአሰልጣኞች ስልጠና የተሳተፉ መምህራን በአይሲቲ የትምህርት ዘርፍ መሰረታዊ ክህሎት በመቅሰምና ልምድ በመለዋወጥ እውቀታቸውን ለሌሎች መምህራንና ለተማሪዎች ለማስተላለፍ እንደሚያስችላቸው ተናግረዋል ::
ስልጠናው ከሁሉም ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ የሳይንስና አይሲቲ መምህራን እንደሚሳተፉ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡
0 Comments