የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ አባላት ከክፍለ ከተማ ምክር ቤት የዘርፉ ቋሚ ኮሚቴ ሰብ ሳቢዎች ጋር በጋራ በመሆን የትምህርት ቢሮን የ1ኛ ሩብ አመት አፈጻጸም ገመገሙ።

by | ዜና

(ጥቅምት 26/2016 ዓ.ም)  ግምገማው በዋናነት የከተማውና የክፍለከተማ ምክር ቤት የሴቶች ህጻናትና  ማህበራዊ ዘርፍ አባላት በትምህርት ተቋማት ባደረጉት የመስክ ምልከታ የተነሱ ሀሳቦችን ጨምሮ ቢሮው በሩብ አመቱ ከእቅድ አንጻር ያከናወናቸው ተግባራት አፈጻጸምን በመገምገም በቀጣይ ከቋሚ ኮሚቴ አባላቱ የሚሰጡ ግብረ መልሶችን  መሰረት በማድረግ ውጤታማ ስራ መስራት እንዲችል ታስቦ መካሄዱን ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ዘይነባ ሽኩር ቢሮው የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል በተለይም ከ6ኛ ፣ 8ኛ እና 12ኛ ክፍል ጋር በተገናኘ ተማሪዎች ውጤታማ እንዲሆኑ እየተከናወኑ የሚገኙ ተግባራት ምን ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ከማየት ባሻገር የመማሪያ መጽሀፎችን ጨምሮ የዩኒፎርምና ደብተሮች ስርጭት ሂደትን በመገምገም የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ ታስቦ ግምገማው መካሄዱን ገልጸው የቋሚ ኮሚቴ አባላቱ በቢሮውም ሆነ በትምህርት ቤቶች ባደረጉት ምልከታ አበረታች ውጤቶችን ማየታቸውን በመጥቀስ  በቀጣይ የተሻለ ስራ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ የትምህርት ስራ የሁሉንም ባለድርሻ አካላት  ሳትፎ የሚፈልግ ተግባር እንደመሆኑ ቢሮው ከተለያዩ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት ላይ እንደሚገኝ ጠቁመው የቢሮው ማኔጅመንት አባላት በየዕለቱ ስራዎችን በመገምገም አቅጣጫ እያስቀመጠ በመሄድ ላይ እንደሚገኝ በመጥቀስ የቋሚ ኮሚቴ አባላቱ ለትምህርት ሴክተሩ ለሚያደርጉት ድጋፍና ክትትል ምስጋና አቅርበዋል።

 

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 0
  • 205
  • 6,046
  • 31,180
  • 147,475
  • 147,475