ENGLISH                                                                                                                                                              የዌብሜይል     መልዕክት ይላኩልንየፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት

መግቢያ

የአገራችንን ትምህርት ልማት በማፋጠን ሌሎች ዘርፎችን ለማሳካት በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ የትምህርት ሥልጠናና ፖሊሲዎች ተቀርጸዋል፡፡ ሆኖም ግን ከሁለት አሥርተ ዓመታት ወዲህ በትምህርት ልማት መስክ እየተደረጉ ያሉት ለውጦችና እንቅስቃሴዎች ተጨባጭ እመርታዎች ፍንትው ብለው እንዲታዩ  ማድረግ ያስቻሉ ናቸው፡፡

በርግጥ የኢፌዲሪ መንግስት የአገሪቱን እድገት ደረጃና ጉዞን ከግምት በማስገባት በየወቅቱ እየተቀረፁ ሲተገበሩ የነበሩት የትምህርት ልማት መርሀ ግብሮች (ESDP) በትምህርት ልማት መስክ ከፍተኛ ለውጥ ማስመዝገብ አስችለዋል፡፡ የትምህርት ልማት መርሃ ግብሮቹ ፡- በአገሪቱ የትምህርት ተደራሽነትን ለማስፈን፣ አግባብነትን ለማስጠበቅ፣ ፍትሀዊነትን በማረጋገጥ፣ ሥርጭትን እውን በማድረግና የትምህርት ጥራትን በማረጋገጥ፣ አይነተኛ ስትራቴጂ በመሆን ውጤታማ መሆን አስችለዋል፡፡

በተለይም የትምህርት ልማት መርሃ ግብሮቹን ከአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ፓኬጅ ነፀብራቅ ከሆኑት ስድስት ፕሮግራሞች ጋር በማጣጣም መተግበር በመቻላቸው አንድ ሁለት ብቻ በመጥቀስ መታለፍ የሌለባቸው በርካታ ለውጦች ታይተዋል፡፡ የስኬት ባለቤትም መሆን አስችለዋል፡፡

የትምህርቱ ሴክተር የምዕተ ዓመቱን ግብ ለማሳካት፣ የትምህርት ልማት ለማፋጠን፡- በመጀመሪያ የትምህርት ተደራሽነትን፣ በመቀጠል ፍትሃዊነትን፣ በሶስተኛ ደረጃ ፍትሃዊነትን ማረጋገጥና አግባብነትን የማስፈን ሥራ የሰራ ሲሆን በ2004 ዓ.ም ግን የትኩረት አቅጣጫ ተደርጎ የተወሰደው የትምህርት ጥራትን ማረጋገጥና አግባብነትን ከግብዓት፣ ከሂደትና ከውጤት አንፃር እየመዘነና ክትትል እያደረገ የትምህርት ልማትን የማፋጠን (ESDPIV) ውጥንን ይዟል፡፡

የአዲስ አበባ /ቢሮ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ት/ቢሮ የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድንና አራተኛውን የትምህርት ልማት መርሃ ግብርን (ESDPIV) በማጣመር በከተማዋ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥና አግባብነትን በማስፈን ስትራቴጂ ቀይሶና ግብ አስቀምጦ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡ ውጥኑን በማሳካት ‹‹በከተማዋ የሰለጠነና የተካነ፣ ስራ ፈጠሪ በዲሞክራሲና መልካም አስተዳደር ግንባታ ሚና ሊጫወት የሚችል ዜጋ የሚያፈራና አገራዊና ዓለም አቀፋዊ ደረጃዎችን የጠበቀ የትምህርትና ሥልጠና ስርዓት ሰፍኖ ማየት›› የሚል ራዕይ ሰንቋል፡፡ ራዕዩን ለመድረስ፡- የትምህርቱ መዋቅር አካላት እንዲሁም በትምህርት መስክ የተሰማሩ ባለሀብቶች ሙያዊ ድጋፍ በመስጠትና አጋር ድርጅቶችን በማስተባብር በትምህርት ሥራ የህብረተሰቡን ባለቤትን በማረጋገጥ፡-

 • ደረጃውን የጠበቀ የትምህርት ስርዓት ማስፈን፣
 • የትምህርት ተቋማትን ማስፋፋትና
 • የከተማውን ተጨባጭ ሁኔታ ያገናዘበና ፍላጎትን መሠረት ያደረገ፣ ቀልጣፋ፣ አሳታፊና ወጪ ቆጣቢ የትምህርት አገልግሎት መስጠት ነው፡፡

የሥርዓተ ትምህርት ዝግጅት ንዑስ የስራ ሂደት

የት/ቢሮውን ራዕይ ተጋርተው፡- የትምህርት ልማትን በማፋጠን እንዲያሳኩ ከተዋቀሩት የሥራ ሂደቶች መካከል አንዱ የሥርዓተ ትምህርት ዝግጅት ንዑስ ሥራ ሂደት ነው፡፡ የሥራ ሂደቱ ቢሮው ያስቀመጣቸውን የትኩረት አቅጣጫዎች በመከተል በከተማዋ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ መተግበር ከሚገባው ተልዕኮ አንዱና ዋነኛ የሆነውን ሥርዓተ ትምህርቱን የማስጠበቅ ኃላፊነት ተጥሎበታል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ት/ቢሮው ያስቀመጠውን የትኩረት አቅጣጫ መሠረት በማድረግ የአፀደ ህፃናት ትምህርትን በከተማዋ የማስፋፋትና ጥራቱን የጠበቀ እንዲሆን የመስራትና ከፍለው መማር የማይችሉትና ችግረኛ ቤተሰብ ህፃናት በመንግስት የቅድመ መደበኛ ት/ቤት ገብተው ለመደበኛ ትምህርት ጥሩ ዝግጅት እንዲያደርጉ ማስቻል ነው፡፡

የጎልማሶችን የኑሮ ደረጃና ማህበራዊ ህይወታቸውን ወደ ተሻለ ደረጃ እንዲደርሱ ለማስቻል ትኩረት ተሰጥቶት በመስራት ላይ ያለውን የተግባር ተኮር የጎልማሶች ትምህርት ተግባራዊነት የሥርዓተ ትምህርት ዝግጅት ሥራ ሂደት እያንቀሳቀሰው ይገኛል፡፡

ከዚህ ላቅ ባለ ደረጃ ዛሬ ላይ መንግስት በከፍተኛ ደረጃ ትኩረት ሰጥቶት እንዲሰራበት ያደረገው የ70 በ30  ትምህርት አሠጣጥ ምጣኔ ስኬታማነት የሳይንስና ሒሳብ ትምህርቶች ሚና ከፍተኛ ነው፡፡ በመሆኑም አገሪቱ መካከለኛ ገቢ ከላቸው ሀገራት ተርታ ለመሰለፍ ለሳይንስና ቴክኖሎጂ የተካኑ ችግር ፈቺና ተመራማሪ ዜጎችን ማፍራት ግድ ይላል፡፡ ይህንን ከወዲሁ በማሳካት ት/ቤቶች በሳይንስና ቴክኖሎጂ ራሳቸውን ተጋላጭ እንዲያደርጉ የሥርዓተ ትምህርት ዝግጅት ንዑስ ሥራ ሂደት የሳይንስና ሂሳብ ትምህርቶች ተማሪውን ተሳታፊና ተመራማሪ (Active Learnning & comperency Based Education) ሆነው እንዲገኙ ጥረት በማድረግ ላይ ነው፡፡

በአለም አቀፍም ሆነ በአገር አቀፍ ደረጃ ትኩረት ተሰጥቶት እተሰራበት ያሚገኘው የአካባቢ ጥበቃ አጀንዳ፡- የስርዓተ ትምህርት ዝግጅት አጀንዳም ሆኖ  በከተማ ባሉ ት/ቤቶች ግንዛቤው እንዲሰፋ እተደረገ ነው፤ በሥርዓተ ትምህርት ደረጃም ተቀርፆ ሀሳቡ እንዲሰፋና እንዲሰርፅ ተደርጓል፡፡

የሥርዓተ ትምህርት ዝግጅት ንዑስ የሥራ ሂደት ተግባር ከላይ የተዘረዘሩት ብቻ አይደሉም፡፡ ለአብነት በልዩ ፍላጎት ትምህርት መስክም ቢሆን ልክ እንደ አካባቢ ጥበቃ ሁሉ (cross-cutting) ተብሎ ሁሌም ወቅታዊና አንገብጋቢ ጉዳይ ተደርጎ በስራ ሂደቱ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

በአጠቃላይ የስራ ክፍሉ ከላይ ለተቀመጡት የትኩረት አቅጣጫዎች ተግባራዊነት‹‹ በከተማዋ አስተዳደር ት/ቢሮ የሚከናወን የመማር ማስተማር ተግባር ተማሪውንና የህብረተሰቡን ፍላጎት በአካቶ መልኩ ጥራት ያለው የመጻህፍት አዘገጃጀትና በአሳታፊ ይዘት በሚካሄደው የመማር ማስተማር ተግባር ውጤታማና መልካም ሥነ-ምግባር ያለው የሰው ኃይል መፍጠር፡፡›› የሚለውን ዓላማ ሰንቋል፡፡ የመርሀ ትምህርት (syllabus) በመረከብ የመማሪያ ማስተማሪያ መጻህፍትንና ትምህርትን በቴክኖሎጂ በሬዲዮና ፕላዝማ በማዘጋጀት ከክልሉ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማጣጣም ያዘጋጃል፣ ያቀርባል፡፡ ጥናትና ምርምርም ያከናውናል፡፡

የሥራ ሂደቱ ደንበኞችና ባለድርሻ አካላት

ደንበኞች                                    ባለድርሻ አካላት

   1. ተማሪ                                   1. መንግስት

2.ወላጆች                                 2. ወላጆች

               3.ህብረተሰብ                            3. መንግስታዊ ያልሆኑ

የሥራ ሂደቱ  ተግባርና ኃላፊነት


 • የፍላጎት ዳሰሳ ያደርጋሉ፣
 • የሥራ ሂደቱ እቅድና በጀት በጋራ ያዘጋጃሉ፣
 • የተዘጋጀውን እቅድ ያፀድቃሉ፣
 • የመሰረታዊና የአፀደ ህጻናት ትምህርት መረጃ ያተናቅረሉ፣
 • መርሃ ትምህርቱን በመፈተሽ፣ በመገምገም ክልላዊ ይዘት ያስይዛሉ፣
 • መርሀ ትምህርቱ ክልላዊ ይዘት መያዙን በካውንስሉ ለማጸደው ለሥራ ሂደቱ ያቀርባሉ፣
 • በሚሰጠውትችት መሰረት ያስተካክላሉ፣
 • የመጻህፍት ዝግጅትና የተለያዩ የመማር ማስተማር ስታንዳርድ ያዘጋጃሉ፣
 • የመጻህፍት ዝግጅት፣ ሕትመት ጥራት ይከታተላሉ፣
 • የሥርዓተ ትምህርቱ አፈፃፀም ድጋፍ፣ ክትትልና ግምገማ ያከናውናሉ፣
 • ለመጻህፍት ሕትመት ስፔስፊኬሽን ያዘጋጃሉ፣
 • መጻህፍት ለተጠቃሚው በትክክል በወቅቱ መዳረሳቸውን ይከታተላሉ፣
 • ሥርዓተ ትምህርትና መማር ማስተማርን በተመለከተ ጥናትና ምርምር ያደርጋሉ፣
 • በጥናቱ ውጤት መሠረት ማሻሻያዎችን፣ አዳዲስ ግኝቶችንና ጠቃሚ መረጃዎችን በማዘጋጀት እንደአስፈላጊነቱ ለት/ቤቶች ያሰራጫሉ፣
 • የሬዲዮ ትምህርት ሥርጭት ይከታተላሉ፣ ይገመግማሉ፣
 • የተለያዩ የሥርዓተ ትምህርቱና የመማር ማስተማር መረጃዎችን ይሰበስባሉ፣

የሥራ ሂደቱ የውስጥ ትስስር (Interface)


 1. ከመምህራንና የትምህርት አመራር ልማት ወሳን የሥራ ሂደት፣
 2. የትምህርት ጥራት ማረጋገጥ ወሳኝ የሥራ ሂደት፣
 3. ከመማር ማስተማር ንዑስ የሥራ ሂደት፣
 4. ከክትትልና ድጋፍ ንዑስ የሥራ ሂደት፣
 5. ከመንግስት ፋይናንስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት፣
 6. ከሰው ኃይል አስተዳደር ደጋፊ የሥራ ሂደት፣
 7. ከፕላን፣ እቅድና በጀት ደጋፊ የሥራ ሂደት፣
 8. ከኮሙኒኬሽን፣ ጉዳዮች ደጋፊ የሥራ ሂደትና
 9. ከኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ ደጋፊ የሥራ ሂደት ጋር ትስስር አድርጓል፡፡

የውጭ ትስስር


 • ከ አዲስ  አበባ  ጤና  ቢሮ
 • ከ ኮተቤ መምህራን ት/ት ኮሌጅ
 • ከ ህጻናት፤ ወጣቶችና ሴቶች ጉዳይ ቢሮ
 • ከ ማህበራዊ ዋስትና
 • ከ ጥቃቅንና አነስተኛ ልማት ኢንተርፕራይዝ ቢሮ
 • ከ TVET ኤጀንሲ ቢሮ
 • ከ ንግድና ኢንዱስትሪ  ቢሮ
 • ከ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ሥራ
 • ከ ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ
 • ከ10ሩ ክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤቶች

ከደንበኞች የሚጠበቁ ቁልፍ ጉዳዮች ምንድናቸው?

 • በትምህርት ዘመኑ ሳይቀደዱ ጥራት ባላቸው ወረቀት የተዘጋጁ ለመማሪያነት ሊያገለግሉ የሚችሉ መጻህፍት
 • ስዕሎችና ፊደላት ግልጽ ሆነው የሚነበቡና ከይዘቱ ጋር የተጣጣሙ ሆነው የተዘጋጁ መጻህፍት
 • እንደየክፍል ደረጃው ከቀላል ወደ ከባድ የተደራጁና የይዘት ተከታታይነት ያላቸው መጻህፍት
 • የመጻህፍቱ ዝግጅት ተማሪዎች በግላቸው ወይም በቡድን የሚያሳትፉ/ አሳታፊ የማስተማር ዘዴን የሚጠቁም ሆነው/የተዘጋጁ መጻህፍት
 • አንድ ለአንድ በሆነ ስርጭት ሁሉም ተማሪዎች /በማንኛውም የት/ቤት ዓይነት የሚማሩ/ የሁሉንም ትምህርት ዓነት መጻህፍት ማግነት
 • ትምህርት እንደተዘጋ ሐምሌ ላይ መጻህፍት ማግኘት
 • የልዩ ፍላጎት ያላቸውን ተማሪዎች መሰረት በማድረግ የተዘጋጁ መጻህፍትና ምዘና ሥርዓት
 • ከመማሪያ መጻህፍት ጋር ተጣጣመና ወቅታዊ ሆነ በጥራት የሚሰማ የሬዲዮ ትምህርት ስርጭት