ENGLISH                                                                                                                                                              የዌብሜይል     መልዕክት ይላኩልንየመምህራንና ትምህርት አመራር ልማት ዳይሬክቶሬት

ትምህርት የአንድ ሀገር ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ማህበራው መስተጋብር በማቀናጀት ለተቀላጠፈ እድገትና ሥልጣኔ የሚጫወተው ሚና ምትክ የለውም፡፡የሀገር ልማት በማፋጠን ከቴክኖለጂና ከሳይንሳዊ ግኝት ጋር ያለውን ትስስር በማጠናከር የህብረተሰቡን አመለካከት በመቀየር ከፍተኛ ለውጥ በማምጣትና ፈጣን ዕድገት ማስመዝግበ የሚችሉ ዜጎች የሚፈሩበት ሲሆን በአግባቡ መያዝና መመራት ይኖርበታል፡፡

በአሁኑ ወቅት በሚደረጉ ዘርፈ ብዙ የልማት እንቅስቃሴ በማጠናከር በአጭር ግዜ ፈጣን ልማት በማምጣት፣ መልካም አስተዳደርና የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ በማፋጠን ውጤት ማስመዝግብ ይኖርብናል፡፡ በመሆኑም የትምህርት ጥራት በማስፈን የሚፈለግብን ድርሻ ለማጫወት የትምህርት ሥርዓታችንን በመገምገም መሠረታዊና ሥርነቀል ለውጥ ማምጣት የሚታለፍ ጉዳይ አይደለም፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በየዘርፍ የመሠረታዊ የስራ ሂደት ጥናት ተካሂዶ መልካም ጅማሮዎች በመታየት ላይ ሲሆኑ በትምህርት ሴክተሩም የሚፈለግብንን ድርሻ ለመወጣት የመሠራታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ ጥናቶች የተካሄዱ ሲሆን ከተጠኑት መካከል የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራር ልማት አንዱ ነው፡፡ ይኸው ጥናት በተወሰ 3 ክፍለ ከተሞች በተመረጡ 9 ቀበሌዎች እንዲሁም በ12 ትምህርት ቤቶች ተካሂዷል፡፡ የእነዚህን ተሞክሮ በማካተት የክልሎችና የትምህርት ሚንሰተር የተለያዩ የጥናት ውጤችንና በትምህርት ቢሮ በተዘጋጀው የክላሰ ቡድን የተሰጡትን ጭብጦችና ጠቃሚ ሀሳብ በማካተት ይህ ሰነድ እንዲዘጋጅ ተደርጓል፡፡

በዚህ ሰነድ የሥራ ሂደቱ ሥያሜ፣ የግብ ስኬተና በጥረት ተደራሽ ግቦች፣ደንበኛና አጋር አካለት፣ የግብዓት-ውጤት-የግብ ስኬት ትስስር፣ የተሰበሩ ህጎችና ስለተገኙ መሰረታዊና ሥር ነቀል ለውጦች፣ የሥራዎች አደረጃጀትና ትስስራቸውን እንዲሁም የሰው ኃይል አደረጃጀት እንዲካተቱ ተደርጓል

  1. የሥራ ሂደቱ ስያሜ፡የመምህራንና የትምህርት አመራር ወሳኝ የሥራ ሂደት
  2. ደንበኛና አጋር አካላት

ደንበኞች /Customers/

የዚህ የሥራ ሂደት ደንበኞች የሚከተሉት ናቸው፡፡

– ተማሪ

– እጩ መምህራን /ሠልጣኞች/

አጋር አካላት (Stakeholder)

የዚህ የሥራ ሂደት አጋር አካላት የሚከተሉት ናቸው፡፡

– ወላጅ

– ህብተሰብ

– መንግሥት

– መያድ

– ቀጣሪ ድርጅቶች

  1. የግብአት- ውጤት- የግብ ስኬት ትስስር

ግብአት (Input)

– ለየደረጃው የሚመጥኑ እና በሥነ-ምግባራቸው፣ በእውቀታቸውና በክህሎታቸው ብቁ የሆኑ መምህራንና የትምህርት አመራር አካላት የማግኘት ጥያቄ፣

ውጤት (Output)

– በየደረጃው በሥነ-ምግባራቸው፣ በእውቀታቸውና በክህሎታቸው ብቁ ሆነው የተሠማሩ መምህራንና የትምህርት አመራር አካላት፣

የግብ ስኬት (Outcome)

– ብቁ ሆነው የተሠማሩ መምህራንና የትምህርት አመራር አካላት በመኖራቸው በእውቀት፣ በክህሎትና በአመለካከት የዳበሩ ውጤታማ ተማሪዎች እንዲፈጠሩ ይደረጋል ::

የሥራ ሂደቱ መጀመሪያና መጨረሻ

የሥራ ሂደቱ ከትምህርት ሚኒስተር መነሻውን ያደርጋል፡፡ ትምህርት ቢሮን ከማዕከል የሚሠሩተንና የራሱን ተጫባጭ ሁኔታ ባገናዘበ የመምህራንና አመራር በማልማት የትምህርት ጥራትን በማስመዝገብ በእውቀት፣ በክህሎትና በአመለካከት የዳበሩ ውጤታማ ተማሪዎች እንዲፈጠሩ የሚደርግበት አሠራር ሲሆን ከላይ እንደተገለፀው ከትምህርት ሚንስተር አስከ ትምህርት ቤት በተያያዥነት የሚወርድ የሥራ ሂደት ነው፡፡

  1. የግብ ስኬትና በጥረት ተደራሽ ግቦች / Desired outcome and stretch objective/

በመጀመሪያ ጥናት ወቅት የግብ ስኬትና በጥረት ተደራሽ ግቦች ተነድፈወቅ የነበረ ሲሆን በሙከራ ትግበራ ወቅት ከተሳተፍ 12 ትምህርት ቤቶች 9 ቀበሌዎችና 3 ክፍለከተሞች የቀረበውን ግብረ መልስ በአግባቡ መቀመጣቸውንና የሚያሰሩ መሆናቸው

በጥረት ተደራሽ ግቦችን ለማስፈፀም በተነደፈው የተለያዩ ተግባራት መካከል በድግግሞሽ ከስርዓተ ትምህርት አቅርቦትና መማር ማስተማር ጋር መያያዛቸው በሙከራ ትግበራ ወቅት የቀረቡ አስተያየቶች መነሻ በማድረግ የማስተካከል ሥራ እንዲሰራ ተደርጓል፡፡

በዚህም መሠረት የተማሪዎች አመራር፣ የልዩ ፍላጎት ትምህርት ባለሙያዎችና የሥነ-ዜጋና ሥነ-ምግባር መምህራን ማልማትና ማሰማራት ላይ በመምህራንና በትምህርት አመራር ልማት ወሳኝ የሥራ ሂደት እንደሰራና ቀደም ብሎ የተያዙት የግብ ስኬትና በጥረት ተደራሽ ግቦች ተፈፃሚነት ላይ መግባባት ተችሏል፡፡

በሌላም ተማሪዎች ከታች ክፍሎች እያሉ /ከ5ኛና በላይ ክፍል ጀምሮ/ ራዕያቸውን እንዲፅፉና መምህር የመሆን ራዕይ ያላቸውን በ”ነገው መምህር” ክበብ እንዲደራጁና ስለመምህርነት ሙያ የትውውቅ ሥልጠና በመስጠት መምረጥ እንዲሁም ተሳትፎአቸውም በተደራጀ መልኩ በትራንስክሪፕታቸው ላይ /ፖርትፎሊዮ/ እንዲቀመጥ በማድረግ ወደ ሙያው ሲገቡ በመረጃነት እንዲያገልግለ ጥቆማ ተሰጥቷል፡፡ በተለይ በቦሌ ክፍለ ከተማ ተጀምሮ ተቀባነይነት አግኝቷል፡፡ ይኸው አሰራር በሌሎች ተደግፎ መሰራጨት ያለበት መሆኑን በእኛም በኩል ስምምነት አለ፡፡