የትምህርት አመራሮችና ባለሙያዎች ግምገማዊ ስልጠና ማጠቃለያ መድረክ መካሄድ ጀምራል፡፡

by | ዜና

አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 5 ፣ 2015 ዓ.ም (ትምህርት ቢሮ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን እቅድ አፈጻጸም እና በ2016 ዓ.ም ዕቅድ ዙሪያ በየደረጃው ከሚገኙ የትምህርት አመራሮች ጋር ለሁለት ቀናት የቆየው ግምገማዊ ስልጠና ማጠቃለያ መድለክ መካሄድ ጀምራል፡፡

በከተማ አስተዳደሩ ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ዋና እና ምክትል ርዕሳነ መምህራንን ጨምሮ ሱፐርቫይዘሮች ፣ ባሉያዎች እንዲሁም የክፍለ ከተማና ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች በውይይቱ የተሳተፉ ሲሆኑ ተሳታፊዎች ለግምገማው እና ውይይቱ በተዘጋጀ የመወያያ ሰነድ ዙሪያ በቡድንና በጋራ በመሆን ሰፊ ውይይት በማካሄድ በማጠቃለያ መድረኩ ላይ መሳተፍ ጀምረዋል፡፡

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 309
  • 374
  • 4,290
  • 15,620
  • 98,486
  • 98,486