አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 10 ፣ 2015 ዓ.ም (ትምህርት ቢሮ) የትምህርት ቴክኖሎጂ መሰረተ ልማቶችን ለ2016 የትምህርት ዘመን ዝግጁ የማድረግ ስራዎች በሁሉም 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ በመከናወን ላይ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አይሲቲ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ደረጀ ዳኜ ገልጸዋል ::
አቶ ደረጀ አክለውም በ2016 የትምህርት ዘመን በዝግጅት ምዕራፍ ውስጥ ከሚከናወኑ ስራዎች መካከል የትምህርት መሰረተ ልማቶች ለ2016 የትምህርት ዘመን ዝግጁ እንዲሆኑ ማድረግ አንዱ መሆኑን ጠቅሰው ጥገናና ጽዳት የሚያስፈልጋቸው መሰረተ ልማቶች በሁሉም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ በባለሙያዎች እንዲጠገኑና እንዲጸዱ በመደረግ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
0 Comments