(ጥቅምት 2/2017 ዓ.ም) የትምህርት ቤት መሻሻል ፕሮግራሞች ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ቀፀላ ፍቅረማርያም ስልጠናውን ሲከፍቱ እንዳሉት ሰልጣኞች መንግስት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በርካታ ሥራዎችን እየሰራ እንደሆነ ተናግረው ከዚህ ውስጥ የትምህርት ቤቶች አካባቢን ምቹ ለማድረግ የተሰሩ ሥራዎች እንዳሉና እነዚህን ሀብቶች በአግባቡ ለመጠቀም እንዲቻል ሰልጣኞች ስልጠናውን በአግባቡ በመከታተል ያላቸውን ቋሚ ሀብት በተገቢ ሁኔታ እንዲጠቀሙና የይዞታ ካርታ የሌላቸው ትምህርት ቤቶችም የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እንዲኖራቸው ሂደቶችን በመገንዘብ በሥራ ላይ እንዲያውሉ አሳስበዋል::
የትምህርት ቤት መሻሻል ፕሮግራሞች ትግበራ ዳይሬክቶሬት የግንባታ ክትትልና ድጋፍ ቡድን መሪ አቶ ሙሉነህ ተክለብርሃን ስልጠናውን ሲሰጡ እንዳሉት ቢሮው የትምህርት ጥራትን ለማምጣት ሰፊ ሥራዎች እየሰራ እንደሆነ ጠቁመው የትምህርት ጥራትን ለማምጣት ምቹ የመማሪያ አካባቢን ማዘጋጀት አስፈላጊና ለመማር ማስተማር ስራው ቁልፍ መሆኑን ተናግረዋል ::
አያይዘውም ትምህርት ቤቶች ምቹ የትምህርት አገልግሎትን ለመስጠት አዳዲስ ግንባታዎች ከመገንባት ባለፈ ያሉትን በአግባቡ ማስተዳደር እንዲችሉ ተማሪዎች መምህራንና የትምህርት ቤቱ ማህበረሰቡ አካላት በቂ ግንዛቤ እንዲይዙ ርእሳነ መምህራን የራሳቸው አስተዋፅኦ እንዲያሳድሩ አሳስበዋል ::
በስልጠናው የቢሮው ባለሙያዎች በ11ዱ ክፍለ ከተሞች የሚገኙ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ የሌላቸው ትምህርት ቤቶች ዋና ርእሳነ መምህራን ፣ የክፍለ ከተማ ትምህርት ቤት መሻሻል ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች ተሳትፈዋል::
0 Comments